በአንዳንድ ሸቀጦች ላይ አለአግባብ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ ንግድ ፍቃድ እስከመሰረዝ የሚያደርስ ቅጣት እንደሚኖር ተገለፀ፡፡

0
974

የኢፌዴሪ ንግድ ሚኒስቴር መንግስት የኑሮ ውድነትን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ለመንግስት ሰራተኞች የደምወዝ ማስተካከያ ማድረጉን ተከትሎ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሸቀጦች ላይ አላግባብ የሆነ የዋጋ ጭማሪ እና በስርጭት ሂደት እጥረት እየተስተዋለ መሆኑን ከተለያዩ የመረጃ ምንጮቸ ለማወቅ ተችሏል። ይህንን ተከትሎ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት በዛሬው እለት የካቲት 28 2009 ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ሚኒስቴር ደኢታ አሰድ ዚያድም ያለውን ሁኔታ እንደሚከተለው ገልፀዋል፡፡

በአገራችን በሚያቀርቡት ምርትና አገልግሎት በዋጋ በጥራት እንዲሁም በአቅርቦት የህብረተሰቡን ፍላጎት ለማሟላት እና ተገቢ የሆነውን ትርፍ ለማግኘት እየተወዳደሩ ያሉ ወይም ጥሩ ፉክክር እያደረጉ ለሀገርም የኢኮኖሚ እድገት ትልቅ አስተዋፅኦ እያበረከቱ ያሉ በርካታ ነጋዴዎች አሉ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ አንዳንድ ነጋዴዎች የነፃ ገበያውን መርህ በሚጥስ አይነት መልኩ ፀረ ውድድር የሆኑ ተግባራትን ሲፈፅሙ ይታያሉ፡፡ በንግዱ መሀበር መካከል ፍትሀዊ የሆነ ውድድር እንዳይኖር የሸማቹን ማህበረሰብ መብትና ጥቅም በሚጥስ መልኩ የመሚንቀሳቀሱ ወይም ሊነግዱ የሚሞክሩ ነጋዴዎች እንዳሉ በንግድ ሚንስቴር እና ሌሎች ተቁዋማት በተደረገ የገበያ ዳሰሳ ለማወቅ ተችሏዋል፡፡

መንግስት ለመንግስት ሰራተኞች ያደረገውን የደሞዝ ጭማሪ ተከትሎ አንዳንድ ነጋዴዎች በአንዳንድ ክልሎች በመሰረታዊ ሸቀጣ ሸቀጦች አለአግባብ ምክንያታዊ ያልሆነ ዋጋ መጨመራቸው ታውቋል፡፡

በዳሰሳው እንደታየው ከሆነ በሸማቹ ላይ አለአግባብ ጫና የሚፈጥሩ ፍትሀዊ ያልሆነ ዋጋን የሚወስኑ እንዲሁም ወቅትና ገበያን እየጠበቁ ዋጋ የሚያን፣ ከመደበኛው ግብይት ስርዓት ውጪ ምርትን በመደበቅ ገበያ ላይ እንዳይወጣ በማከማቸት አርቴፊሻል የሆነ እጥረትን በመፍጠር ሸማቹ ማህበረሰብ ላይ ችግር የሚፈጥሩ ወይም አለአግባብ ጥቅም ለማግኘት የሚሞክሩ ነጋዴዎች እንዳሉ ታይቷዋል፡፡ ከስነ ልክ ጋር ተያይዞ ማለትም የልኬት መሳርያዎችን በማዛባት ሸማቹን ማህበረሰብ ለማጭበርበር የሚሞክሩ እንዳሉም ታውቋል፡፡

እነዚህን ችግሮች ህገወጥ እና እርምጃ የሚያስወስዱ በመሆናቸው የተለያየ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል፡፡ የምንከተለው የነፃ ገበያ ኢኮኖሚ ስርዓት በመሆኑ ነጋዴው በነፃ መወዳደር መቻል አለበት፡፡ ይህ ማለት ግን እንደፈለጉ ዋጋን መጫን ሳይሆን በጥራት በዋጋ እና አቅርቦታቸው ተወዳድረው ተገቢውን ትርፍ ማግኘት የሚችሉበት ስርአት እንደመሆኑ መጠን ነጋዴው በፍትሀዊነት መወዳደር መቻል አለበት፡፡

ችግር በመፍጠር እያሉ ባሉ አንዳንድ ነጋዴዎች መንግስት ንግድ ፍቃድን እስከመሰረዝ ያለ እርምጃን ይወስዳል፡፡ እንደሚታወቀው በየደረጃው በተለይ በአዲስ አበባ መሰራታዊ ሸቀጦችን በመደበቅ ገበያ ላይ ችግር የፈጠሩ ነጋዴዎች በአስተዳደሩም እርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡ ሸማቹ እንዲሁም ነጋዴው መሀበረሰብ እነዚህ ችግር ፈጣሪ ነጋዴዎችን ማጋለጥ ለዚህም በ8478/ 8077 የነፃ ስልክ መስመሮች በመጠቆም ተጠያቂ እንዲሆኑና ህግና ስርአት እንዲከበር ማድረግ አለባቸው፡፡ በአዲስ አበባ እና በየክልሉ የሚገኙ የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣናት፣ ተቁዋማት እና የንግድ ቢሮዎች ተገቢውን የሆነ ክትትል እያደረጉ የእርምት እርምጃ መውሰድ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የንግድ ሚኒስቴርም በቀጣይ በተደራጀ መልኩ የተጠናከረ እርምጃን ይወስዳል፡፡

በዘላቂነት ችግሩን ለመፍታት የንግድ ሚኒስቴር በሁሉም ክልሎች ደረጃ ተግባራወዊ እየሆኑ ያሉ ጥቅሎችን በመቅረፅ በአገር ደረጃ ስራ ላይ እንዲውሉ አድርጓል፡፡ ይህንንም የሚከታተሉ አደረጃጀቶች በክልሎች እንዲፈጠሩ ተደርጓል፡፡  ቢሆንም ግን በአሰራር ላይ ክፍተቶች አሉ፡፡ ይህንንም ክፍተት ለመድፈን ሚኒስተሩ የተጠናከረ ስርዓት ለማካሄድ ይጥራል፡፡

 

አቶ ኑረዲን መሀመድ በንግድ ሚኒስቴር የአክስዮንና የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ጉዳይ ክትትል እና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተርም በበኩላቸው የሚከተውን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ከሰሞኑ ከዚህ ከንግድ እና ዘርፍ ምርጫ ማህበራት ምርጫዎች ጋር ተያይዞ እየታዩ ያሉን ችግሮች በተመለከተ የንግድ ሚኒስቴር እስካሁን ያለውን መረጃዎች እና አክስዮን ማህበራት ላይ እየተሰራ ያለውን ስራ እናያለን፡፡

የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቶች ሁለት አፔክስ ያለው ሲሆን የኢትዮጵያ የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ደግሞ ዋናው ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ በየክልሉ የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት  ምክር ቤቶች እና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቶች አሉ፡፡ የንግድና ዘርፍ ምክርቤት ማቋቋሚያ አዋጅ 3/41/1995 እነኚህን ማህበራት የማደራጀት፣ የመከታተል የመቆጣጠር ስልጣንን ለንግድ ሚኒስቴር ነው የሰጠው፡፡ በ2003 ንግድ እና ንግድ ኢንዱስትሪ በሁለት ቦታ ከተለያዩ በኋላ በአስፈፃሚ አካላት ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ የንግድ ዘርፍን በተመለከተ ንግድ ሚኒስቴር እየመራ ሲሄድ የኢንዱስትሪ ዘርፎች ደግሞ በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ስር እየተደራጁ እንዲሄዱ ተደርጓል፡፡ በ2009 የኢትዮጵያ ንድግ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ምርጫን አስመልክቶ ከየክልሉ ቅሬታዎች እየቀረቡ ይህ ምርጫ አልተካሄደም፡፡ በዚህም የንግድ ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ አዋጅ በግልፅ ያስቀመጠው በተዋረድ በታች የሚገኙ በክልል፣ በዞን፣ በከተማ፣ በወረዳ የሚገኙ ምክር ቤቶች አሳታፊና ፍትሃዊ የሆነ ምርጫ ማከናወናቸው ሲረጋገጥ የኢትዮጵያ ንድግ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ምርጫውን ያከናውናል፡፡

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.