የሳምንቱ የሊጉ ታላቅ ጨዋታ በቅ/ጊዮርጊስ የበላይነት ተጠናቋል።

0
913
picture from: Yonas Gutama

በ17ተኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች በእረፍት ቀናት የተካሄድ ሲሆን በሜዳቸዉ ከተጫወቱ ስምንቱ ክለቦች ሰባቱ ኣሸንፈዋል።ብቸኛዉ ክለብ ባለሜዳ ወልዲያ ኣቻ ወቷል።  ቅዳሜ እለት በከፍተኛ ጉጉት ሲጠበቅ የነበረዉ የቅዱስ ጊዮርጊስና የደደቢት ጨዋታ 10 ሰኣት ሲል ጅማሮን ሲያደርግ የፈረሰኞቹ ተጫዎች የሆነዉ ሳላዲን በርጌቾ ለቀድሞ ኣሰልጣኙ ማስታወሻ ስጦታ ኣበርክቷል።  ጨዋታዉ የሊጉን የዋንጫ ፉክክር ማጥበብና ማስፋት የሚችል በመሆኑ ሀይልና ሽኩቻ የበዛበት ከባድ ጨዋታ ነበር ።ሆኖም ግን በሁለቱም ክለቦች በኩል በተለያየ የጨዋታዉ ጊዜ እየተለዋወጡ የጨዋታዉን ሀይል ወደራሳቸዉ በማድረጋቸዉ ተመልካቹ በጎል ብቻ ሳይሆን በጨዋታዉ ተዝናንቶ እንዲወጣ በማስታቻል ቅዱስ ጊዮርጊስ 3 ለ2 ኣሸንፎዋል። በደደቢት ቡል ብርሃኑ ቦጋለን በቀይ ኣቷል።በጨዋታዉ ሂደት የቅ /ጊዮርጊስ ደጋፊዎች በዘንድሮ ኣመት ያሳዩትን ኣደጋገፍ በዚህም ጨዋታ ደግመዉታል።ሌላዉ ሊጠቀስ የሚገባዉ በስነ ምግባራቸዉ ኣርኣያ ሊሆኑ የሚችሉ ተጫዎቹ በሜዳ ዉስጥ ኣላስፈላጊ ድርጊት ሲያደርጉ ተመልክተናል።ደጋፊዉም ይህን እኩይ ተግባር ሊያወግዝ ሲገባዉ ለስድብ መጋበዙ ተገቢ አይደለም እንላለን።

በመቀጠል በሊጉ የተደረጉት ሰባት ጨዋታዎች በእለተ እሁድ የተካሄድ ናቸዉ። በዚህ ሳምንት ሌላዉ ይጠበቅ የነበረዉ የይርጋለሙ የሲዳማና የኣዳማ ጨዋታ ነዉ ።ሁለቱ ክለቦች ከጨዋታዉ ኣስቀድሞ የነጥብ ልዩነታቸዉ ኣንድ የነበረ ሲሆን የደረጃ ልዩነት መፍጠር የሚችል ጨዋታ ነበር።ነገር ግን የነበረዉን ልዩነት ማስፋት የቻለዉ ባለሜዳዉ ሲዳማ ቡና 1 ለ0 በማሸነፍ ወደ ዋንጫ ፉክክር ያለዉን ግስጋሴ ኣስቀጥሏል። ወልዲያ ያቀናዉ አርባምንጭ ከነማ በሊጉ የሳምንቱን ብቸኛዉን የኣቻ ዉጤት ይዞ ተመልሶል ።አሁንም ወልዲያ በሜዳዉ መሸነፍ ያልቻለ ክለብ ሆናል። ጅማ ላይ ኣዲሱ ኣሰልጣኝ ኣስራት ኣባተን የቀጠረዉ ኣዲስ ኣበባ ከነማ በጅማ ኣባቡና 1 ለ0 በሆነ ዉጤት ተሸንፎ መቷል።በታሪኩ የመጀመሪያዉን የሊጉን ጨዋታ በሽንፈት ጀምሮል ኣሰልጣኙ። የተወሰኑ ተጫዎችንና በኣጨዋወት ዘይቤ የተለየ ኣቀራረብ ይዞ የመጣዉ የዉበቱ ኣባተ ሀዋሳ ከነማ ወራጅ ቀጠና ላይ የሚገኝዉን ንግድ ባንክን ኣስተናግዶ 4 ለ0 በማሸነፍ ወደ መሀል ሰፋሪነት ያለዉን ጉዞ ኣስቀጥሏል።  ወደ ሶዶ ያቀናዉ ፋሲል ከነማ በሁለተኛዉ ዙር ጨዋታዎች ማሸነፍ ኣልቻልም ትናንትም 2 ለ1 በሆነ ዉጤት በወላይታዱቻ ተሽንፉል።ቀስ በቀስም ወደታች እየተሸራተተ ይገኛል ።

ብቸኛዉ የኣዲስ አበባ የዘጠኛ ሰኣት ጨዋታ የነበረዉ በሳምንቱ በኢትዮ ኤሌክትሪክ የሰፊ ጎል ልዩነት 3 ለ1 በማሸነፍ ከተደጋጋሚ የኣቻ ዉጤት በኋላ የተላቀበተን ዉጤት ኣስመዝግቦል። ይህን ጨዋታ ተከትሎ ምሽት ላይ በደጋፊዎች ቁጥር እና በማራኪ ጨዋታ የተሞላበት የሳምንቱ መዝጊያ ጨዋታ ኢትዮጱያ ቡናና መከላከያ አገናኙታል።ጨዋታዉ ብዙ የማግባት እድል የፈጠረዉ ኢትዮጱያ ቡና ጥሩና ከመከላከያ የተሻለ እንቅስቃሴ በማሳየት 4 ለ0 ኣሸንፎል ።ሁለቱ ግቦች በፍፁም ቅጣት ምት የተገኙ ናቸዉ።በጨዋታዉ ሂደት በሀይሉ ግርማ የቀይ ካርድ ሰለባ ነበር።በኢትዮጱያ ቡና በኩል ወደ መሪዎቹ የሚያስጠጋዉን ዉጤት ያመጣበት የሳምንቱ የመጨረሻ ጨዋታ ነዉ። ፈረሰኞቹ እንደባለፈዉ ሳምንት ሁላ መሪነታቸዉን ኣጠናክረዉ ይዘዋል።እሱን በመከተል በሁለተኛዉ ዙር የተጠናከዉ ሲዳማ በኣራት ነጥብ ዝቅ ብሎ ይከተላል።በጊዮርጊስ የተሸነፈዉ ደደቢትም በጎል ክፍያ ቡናን በልጦ በሶስተኝነት ተቀምጦል። የኮከብ ግብ አግቢዎቹ በዚህ ሳምንት ፋክክራቸዉን እንደቀጠሉ ናቸዉ ።ጌታነህ 12 ግብ መሪነቱን የያዘ ቢሆንም ከሰሞኑ ወደ ኣግቢነት የመጣዉ ሳላዲን ሰይድ ከክለቡ አጋሩ ኣዳና ግርማ ጋር በ9 ግቦች ይከተላሉ።

በዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.