በ17 ተኛዉ ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች በሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ መሪዎቹን በማገናኝት ዛሬ ቅዳሜ ይጀምራል።

0
948

በኢትዮጱያ ፕሪሚየም ሊግ 17 ተኛዉ ሳምንት ጨዋታዎች ቅዳሜና እሁድ በአአ ሶስት ጨዋታዎችና በየክልሉ በሚካሄድ አምስት ጨዋታዎች ቀጥሎ ይዉላል።  ዛሬ ቅዳሜ በብቸኝነት የሚደረገዉ ጨዋታ 10 ሰአት ሲል የሊጉን መሪዎች ያገናኛል።ቅዱስ ጊዮርጊስ ከደደቢት ። በዛሬዉ ጨዋታ ባለሜዳዉ ፈረሰኞቹ ሲሆኑ በመጀመሪያዉ ሳምንት ጨዋታ ጊዮርጊስ ማሸነፎ የሚታወስ ነዉ 2 ለ0 በሆነ ዉጤት ።በሊጉ ከ2002 ጀምሮ( ደደቢት ወደ ሊጉ የመጣበት ጊዜ ኣንስቶ) ለ15 ጊዜ ሁለቱ ክለቦች የተገናኙ ሲሆን 11 ጊዜ ያሸነፈዉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነዉ ፤ደደቢት ሶስቱን ጨዋታ አሸንፋል ።ኣንድ ጨዋታ ብቻ ከ15 ዉስጥ ኣቻ የወጡት።የዛሬ ግንኙነታቸዉ ሁለቱም በመሪዎቹ ተርታ ኣንደኛና ሁለተኛ ተቀምጠዉ መሆኑ ይበልጥ ተጠባቂ ያረገዋል።በግብ ኣግቢዎቹ በኩል በሊጉ ከፍተኛ ግብ ኣግቢ ያሉት በሁለቱ ክለቦች መሆኑ ይበልጥ ተጠባቂ ያደርገዋል ።ጌታነህ ከበደ ኣዳና ግርማና ሳላዲን ሰይድ ይጠቀሳሉ።

ቀሪ ሰባት ጨዋታዎች በእለተ እሁድ ሲካሄድ ሁለቱ አአ ስታድየም ሲደረግ አምስቱ የክልል ጨዋታዎች ይሆናሉ ። ሌላዉ በዚህ ሳምንት ከመሪዎቹ ተርታ ተቀምጦ የሚገናኙዉ ጨዋታ ይርጋለም ላይ ይጠበቃል።ሲዳማ ና ኣዳማ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ በኣንድ ነጥብ ተለያይተዉ 3 ተኛና ኣራተኛ ላይ ተቀምጠዉ የነገዉ ጨዋታቸዉን ያስተናግዳሉ።  በሼህ ሁሴን ኣሊ ኣሙዲን ስታድየም ወልዲያ ከነማ ባለፈዉ ሳምንት በሊጉ በሰፊ ጎል የተሸነፈዉ አርባምንጭ ከተማ ጋር ይጫወቷል።

ሀዋሳ ላይ ሀዋሳ ከነማ ከኢትዮጱያ ንግድ ባንክ ይጫወታሉ።የመጀመሪያ ዙር የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ በክብርኣለም ዳዊት ድንገተኛ ህልፈት ምክንያት ጨዋታቸዉ ተራዝሞ እንደነበር እናስታዉሳለን።  በኣባ ጅፋራ ከተማ ደግሞ ጅማ ላይ ሁለቱ በዘንድሮ ወደ ሊጉ ያደጉት ክለብ ያገናኛል።ጅማ ኣባቡና ከኣዲስ ኣበበ ከተማ።የሚገርዉ ሁለቱም ክለቦች የኣሰልጣኝ ለዉጥ አርገዉ የሚያደርጉት ጨዋታ ነዉ።በተለይ የኣዲስ አበባዉ ኣሰልጣኝ ኣስራት ኣባተ የመጀመሪያዉ የሊጉ ጨዋታ በታሪኩ ያደርጋል። የመሳይ ተፈሪዉ ወላይታ ድቻ ሶዶ ላይ ፋሲል ከነማን ያስተናግዳል።ጨዋታዉ ለሁለቱም ወሳኝ ሲሆን በፋሲል በኩል ጨዋታዉን የሚያሸንፍ ከሆነ ለተፎካካሪነት ያለዉ ሂደት የሚያስቀጥል ይሆናል።በባለሜዳዉ ድቻ በኩል ደግሞ ነጥቡን ኣሻሽሎ ራሱን በሊጉ የሚያቆየዉን ነጥብ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል።አአ ላይ ብቸኛዉ የዘጠኝ ሰአት ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪን ከድሬዳዋ ከነማ ያገናኛል።ሁለቱም ክለቦች በ16ቱ ሳምንት ጨዋታዎች በእኩል 16 ነጥብ ተቀምጠዉ ነዉ የሳምንቱን ጨዋታ የሚያደርጉት።ይህን ጨዋታ ተከትሎ በሳምንቱ የመጨረሻና ተጠባቂዉ ጨዋታ ይካሄዳል።ኢትዮጱያ ቡና ከመከላከያ በ11:30 ላይ ።ሁለቱም ክለቦች ኳስን ይዘዉ የሚጫወቱ ሲሆን ጨዋታቸዉ ማራኪ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።በመጀመሪያ ዙሩ ጨዋታ 2 ለ2 በሆነ አቻ ዉጤት መጠናቀቁ የሚታወስ ነዉ ። ሁሉም የክልል ጨዋታ ዘጠኝ ሰኣት የሚካሄዱ ናቸዉ።

በዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.