የ2009 አ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች ቅዳሜና እሁድ ተደርገዋል።

0
1156

የሁለተኛ ዙር የመክፈቻ ጨዋታ የነበረዉ ቅዳሜ እለት በተደረገዉ የ9 ሰአት ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከወልዲያ ከነማ ያደረጉት ነበር ።በጨዋታዉ ንግድ ባንክ ለሶስት አመታት ያሰለጠነዉ ኣሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነ ማርያምን ካሰናበተ በኋላ ያደረገዉ ጨዋታ ነበር ።በዉጤቱም ያለ ግብ አቻ በመለያየት የዙሩን ጅማሮ አድርገዋል።እነሱኑ ተከትሎ ጥሩ ፋክክር ይኖራል ተብሎ የተጠበዉ የ11:30 ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከጅማ አባቡና ነበር ።

ወደ ጅማ ኣባቡና ኣሰልጣኝነት ከመጣ በኋላ ገብረ መድህን ሀይሌ የመጀመሪያዉ የአዲስ አበባ ጨዋታ ነበር ከኤሌክትሪክ ጋር ያደረገዉ።በመጀመሪያ ዙር አብዛኛዉ ጨዋታ በኣቻ የተለያየዉ ኤሌክትሪክ በሁለተኛዉም ዙር የኣቻ ዉጤቱን የሚያስቀጥል ነጥብ ይዞ ወቷል በቅዳሜ ጨዋታ። ይህም እንደ ፊተኛዉ ያለ ግብ ኣቻ ያለቀ ጨዋታ ነዉ። በእለተ እሁድ ቀሪዎቹ ስድስት ጨዋታ የተካሄድ ሲሆን ሶስቱ ከኣዲስ አበባ ዉጪ የተካሄድ ነበሩ ።ሌሎቹ ሶስቱ ደግሞ ዋናዉ ከተማ ላይ የተደረጉ ናቸዉ። በዚህ 16 ሳምንት ጨዋታዎች ግቦች ያስተናገዱት ጨዋታ አራት ሲሆኑ ሶስቱ የክልል ጨዋታዎች ናቸዉ። ጎንደር ላይ ከሜዳ ዉጪ የሄደዉ ሲዳማ ቡና 3 ለ1 በሆነ ዉጤት መርታት በመቻሉ አሁንም በሊጉ እየተፍካከረ እንደሚገኝ ኣሳይቷል።ከሀዋሳዉ የአፋሪካ ቻንፕየንስ ሊግ ጨዋታ በኋላ ወደ አርባምንጭ ያቀናዉ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሳምንቱ በሰፊ ጎል ያለቀ ጨዋታ ዉጤት 4 ለ1 ኣሳክቶ መቷል።በጨዋታዉ መጠናቀቅ በኋላ የተወሰኑ ግርግሩች እንደነበሩም ሰምተናል።

በቅርብ ኣሰልጣኙን ለብሄራዊ ቡድን ኣሰልጣኝነት ያሾመዉ ኣዳማ ከነማ ወደ ድሬዳዋ አቅንቶ በሳምንቱ በሊጉ በብቸኝነት በግብ ኣቻ የተጠናቀቀ ጨዋታ እንዲሆን ሆናል።1 ለ1 በሆነ ዉጤት።  እረፍት የሌለዉ አአ ስታድየም እሁድ ለትም ሁለት ጨዋታዎችን ያገናኝ ሲሆን ዘጠኝ ሰአት የተካሄደዉ ጨዋታ በሳምንቱ በጉጉት ሲጠበቅና በእለቱም ብዙ ተመልካች ወደ ስታድየም የከተመበት ጨዋታ ነበር ።ነገር ግን የተጠበቀዉን ያህል የተሻላ እንቅስቃሴ በሁለቱም ክለቦች በኩል ሳንመለከት ወተናል።ደደቢት ከኢትዮጱያ ቡና በታሪካቸዉ በሊጉ ለመጀመሪያ ጊዜ አቻ ተለያይተዋል ።በጨዋታ የእረፍት ሰአት ላይ የደደቢቱ አንጋፋ አሰልጣኝ አስራት ሀይሌ ከደጋፊዎች ጋር እሰጣ ገባዉ ዉስጥ ገብተዉ ነበር ፤አልፎም ለቦክስ ሲጋበዙ ተመልክተናል።ሌ ላዉ አሁንም በኢትዮጱያ ቡና ደጋፊዎች ያስተዋልነዉ ነገር ስም እየተጣሩ ስድብ በስታድየሙ ቀኝ ጥላፍቅና ግራ ላይ ማስተዋል ችለናል።ተጫዋቾም ደጋፊን ላልተገባ ድርጊት የሚዳርግ ሜዳዉስጥ ከማድረግ ቢቆጠቡ በዚህ አጋጣሚ መልካም ነዉ እንላለን።

የአዲስ አበባዉ አበበ ቢቂላም አአ ከነማን ከሀዋሳ ከነማ ያስተናገደበት የ10 ሰአት ጨዋታ ነበር ።በጨዋታዉም የመጀመሪያዉን ዙር ዉጤት መቀልበስ የቻለበትን ድል አስመዝግባል፤ ሀዋሳ ከነማ 1 ለ 0 በሆነ ዉጤት። የሳምንቱ የመዝጊያ ጨዋታ የነበረዉ የ11:30 የአአ ስታድየም ጨዋታ ነዉ ።በከፊል ዝናብና ጭጋጋም በነበረዉ አየር የተጫወቱት መከላከያና ወላይታ ድቻ ነበሩ።በጨዋታዉም ጥሩ የመሸናነፍ ነገር ቢታይባቸዉ የማታ የማታ ከጎል ድርቅ ያልወጣዉ አአ ስታድየም አራተኛዉን 0 ለ0 ያለቀ ጨዋታ አስተናግዶ የ16 ተኛዉ ሳምንት ጨዋታዉን ዘግቷል። አሁንም ግስጋሴያቸዉን የቀጠሉት ፈረሰኞቹ በ32 ነጥብ ከፊት ተቀምጠዋል ።ጊዮርጊስን በመከተል አሞራዎቹና ሲዳማ በ28 ነጥብ በተከታታይ ተቀምጠዋል። የመጨረሻ ግርጌ ላይ የዋናዉ ከተማ ክለብ የሆነዉ አዲስአበባ ከነማ 16 ላይ በ10 ነጥብ ተቀምጧል ።ከእሱ በላይ ጅማ አባቡና ንግድ ባንክ በእኩል 14 ነጥብ አለን እያሉ ይገኛሉ።  የግብ አግቢነቱኑ ጌታነህ ከበደ 11 ጎሎች ኣዳነ ግርማ በ9 ግቦች ይከታላል ከኣዳና በሁለት ግቦች ዝቅ ስንል ሳላዲን ሰኢድን ና ፍፁም ገ/ማርያምን እናገኛዋለን።

በዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.