ጥቂት በቅርቡ ስለተመረጠዉ የኢትዮጵያ ወንዶች ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ አሸናፊ ከበደ ።

0
1122

በ1952 አመተ ምህረት የተወለደዉ በኦሮሚያ ክልል በምትገኝ ቱሎ ቦሎ ዉስጥ ነዉ።እግር ኳስ በክለብ ደረጃ ተጫዉቶ ያሳለፈ ሲሆን ወደ ኣሰልጣኝነትም የገባዉ በድንገትና በኣጋጣሚ መሆኑን ይናገራል።ወቅቱ 1982 ነዉ፡፡ ለክለቦች በመጣ የአሰልጣኝነት እድል ፤ክለቡም ባንክ አሸናፊን በመምረጡ አሰልጣኝነቱን ሀሁ ብሎ ጀመረ ።በአሰልጣኝነት ህይወቱም 26 አመታት በተለያየ ቦታ አሳልፎል።ለመጥቀስ ያክል ባንኮች፣ መከላከያ ፣ሲዳማ ቡና እና ኣዳማ ከነማ አሰልጥኑዋል።

በብሄራዊ ቡድን ደረጃ ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ በሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ተሳታፊ የነበረዉን የኢትዮጱያ ብሄራዊ ቡድን ኣሰልጣኝ ነበር። በክለቦች ቆይታ ረጅም ጊዜ በመቆየት ያሰለጠነበት ክለብ ኢትዮጱያ ባንኮችአሸናፊ ሲጠራ ባንኮች መጥራት ግድ ይለናል ። ለ6 አመታትም በክለቦች ተጫዉቶ ያለፈ እና የክለቡ አምበልም ሆኖ ያሰለፈባቸዉ ጊዜያት አይዘነጉም ።  በቅርብ ሶስትና አራት አመታት ዉስጥ አሸናፊ በቀለን በኣዳማ ከነማ ዉስጥ ስኬታማ ጊዜ እያሳለፈ የሚገኝ አሰልጣኝ ነዉ።

በተለይ ቡድኑ ከታችኛዉ ሊግ ከመጣበት ወቅት ጀምሮ በመጀመሪያዎቹ ተርታ መቀመጥና ተፎካካሪ እንዲሆን ያስቻለ ሰዉ ነዉ።ነገር ግን በሌሎች ክለቦች ባሳለፈባቸዉ ጊዜያት የአሸናፊ ቡድን የመጀመሪያ ዙር ላይ ጠንካራና ተፎካካሪ ይሆንና በሁለተኛዉ ዙር የቀድሞን ነገር መድገም እንደሚከብደዉ አብዛኛዉ የእግር ኳሱ ተመልካች ይናገራል።

በዘንድሮ የሊጉ ዉድድር አዳማ ከነማ ከመሪዎቹ ተርታ ተቀምጦ የመጀመሪያዉን ዙር የጨረሰ መሆኑ ይጠቀሳል። እናም በሊጉ ካሉት ከሚጠቀሱት አንጋፋ አሰልጣኞች የሚጠቀሰዉ አሸናፊ በቀለ ከቀናት በፊት የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ቴክኒክ ኮሚቴ እሱን ለብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ መምረጡንና ስራ ኣስፈፃሚዉ ማፅደቁን ሰምተናል።ነገር ግን ስለ ስምምነታቸዉና ጠቅለል ያለዉ በጋዜጣዊ መግለጫ እናገራለሁ ብሏል እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ።

በመጨረሻም የስፖርት ክፍላችን በቀጣዩ ጊዜ ለሚገጥመዉ ነገር ሁሉ መልካሙን ይመኛል።

አንዳንድ መረጃ፡  ከሀበሻ ስፖርት መፅሄት ቁጥር 3

በ ዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.