ሲሸልስ የተጓዘዉ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ሶስት ነጥብ አሳክትዋል

0
863

በዳግም ታምሩ

በኢትዮጵያ ታሪክ በተደጋጋሚ በመሳተፍ የሚታወቀዉ ቅዱስ ጊዮርጊስ እንደ ሀገር ቤት ዉድድር የበላይነት ባይኖረዉም የተሻለ ዉጤት ማለት ረጅም ጉዞ የተጓዘዉ በ2005 አም በጀርመናዊ አሰልጠኛ በክሩገር ዘመን መሆኑ የሚታወስ ነዉ ።

በዘንድሮ ተሳትፎ ደግሞ ቅዱስ ጊዮርጊስ በቻንፕየንስ ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታ በዛሬ እለት  አካሄዶ ሲሸልስ ቪክቶሪያ ላይ ኮትዲኦሮን በሳላዲን ሰኢድ ሁለት ግቦች 2 ለ0 በማሸነፍ የመጀመሪያዉ ሶስት ነጥብ አግኝቷል ።ወደ ስፋራዉ ባለፈዉ ሀሙስ እለት ተጫዎችና የተወሰነ ቁጥር ያላቸዉን ደጋፊዎችን ይዘዉ በቻርተር አዉሮፖላን የተጓዘ ሲሆን ።በቀጣይ ሳምንት የካቲት 12 ሀዋሳ ላይ  የመልሱን ጨዋታ የሚያስተናግድ ይሆናል።።ፈረሰኞቹ ይህን ጨዋታ በደርሶ መልስ ካሸነፋ።የ ዮሜስ ደሉም ና የሊዮፓሮድ   አሸናፊ የሚገጥም ይሆናል።

ሌላዉ በአፍሪካ መድረክ ተሳትፎ የሚያደርገዉ መከላከያ ነዉ ።መከላከያ ወደዚህ የዉድድር መድረክ የደረሰዉ ኢትዮጱያ ጥሎ ማለፍ ዉድድር አሸናፊ በመሆኑ ነዉ።የሚገርመዉ መከላከያ በዚህ ዉድድር ለሁለት ተከታታይ ወቅቶች ተሳትፎ ቢያደርግም በሁለቱም ጊዜ በመጀመሪያዉ ዙር ከዉድድሮ በጊዜ ወቷል ።

በዘንድሮ ተሳትፎዎቸዉ ደግሞ በነገዉ እለት በ10 ሰአት አአ ላይ የካሜሮን ክለብ የሆነዉን ያንግ ስፖርት አካዳሚ  ያስተናግዳል።መከላከያ ይህ ጨዋታ በደርሶ መልስ ካሸነፈ ሴፋክሲያን የሚገጥም ይሆናል።

በመጨረሻ ኢትዮጱያን ወክለዉ በኣፋሪካ መድረክ ለሚሳተፋት ክለቦቻችን መልካም እድል እንዲገጥማቸዉ ድረገፃችን በዚህ አጋጣሚ ይመኛል ።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.