ተስፋዬ ለማ “የባህል ሙዚቃው አባት “

0
1245

የሀገራችን በተለይ የባህል ሙዚቃ ላይ ትልቅ አሻራ ያለው ሰው ነበር ። በተለይ ወደ ሙዚቃ የገባው፤ ተማሪ ቤት ማለትም ተፈሪ መኮንን እየተማራ በነበረበት ወቅት በጊዜው በህዝብ በአላት ትርኢት የሚያሳይቱን ሰልፈኛ ሙዚቀኞችን በሚመለከትበት ጊዜ ነበር ልቡ ወደ መዚቃ የሸፈተው፤ሸፍቶም ዝም አላላም ወደ ሚለማመዱበትስፍራ በማቅናት የሙዚቃውን መሪ ጠይቆ ወደ ሰልፈኞቹ ተቀላቅሉ ሙዚቃን ሀሁ ብሎ ጀመረ ።ተስፋዬ ለማ፤ ይህን ታላቅ ሰዉ ካጣናዉ ነገ ጥር 24 አራት አመት ሞላዉ። ይህን በማሰብ ጥቂት ከሰራቸዉ ስራዎች ለማስታወስ በማሰብ ዛሬ ዘከርነዉ።

የባህል ሙዚቃ ሲነሳ መዘንጋት ከማይገባቸው ሰዎች ውስጥ አንድ ሰዉ በሻህ ተክለማርያም ተጠቃሽ ናቸው ።እኝህ ሰው መነሻ ነገር በወቅቱ የንጉሱ እንደራሴ በነበሩት መኮንን ሀብተወልድ በኩል ነበር ተመርጠዉ በባህል ሙዚቃ ላይ እንዲሰሩ የተደረጉት ።በተለይ ወደ ውጪ በሚሄዱበት ጊዜ የአውሮፖን ሙዚቃ መሳሪያ በህብረትና በአንድነት ለንጉሱ ክብር ሲጫወቱ ተመልክተው ፤እኛም እኮ አለን የራሳችን የሙዚቃ መሳሪያ በማለት ሀሳባቸውን ለበሻህ ይነግሩታል። በወቅቱም በሻህ የዳግማዊ ሚልኒክ ት/ቤት የቫዮሊን ተማሪ የነበሩ ሲሆን እና በአቅራቢ በሚገኝ መዘመራን በማሰባሰብ የኢትዮጱያን ባህላዊ ሙዚቃ በማቀናጀት አሀዱ ብለው ጀመሩ። . . ወደ 1966 አም ገደማ ደግሞ ከአሜሪካ በመጡ መምረህራን ሀሳብ አመንጭነት በተለይ ሀሊም አልዳባ በተባለ የሙዚቃ አዋቂ ከ40 በላይ የኢትዩጱያ ሙዚቃ ተጫዎችን በማሰባሰብ በቀድሞ በቀኃሥ ዩኒቨርስቲ በ አሁኑ አአዩ ኦርኬስትራ ኢትዮጱያ ተመሰረተ ። ለአመታት በመሰራቾቹ ቢመራም ነገር ከሀሊም አልዳባ ጋር ተያይዞ ስለኦርኬስትራው ስማቸው ከሚጠሩ ሰዎች ውስጥ ዋነኛው ሰው ተስፋዬ ለማ ነው። ኦርኪስተራውን ከ1973 -1982 አም ከውጪ ሀገር ዜጉች ጋር በመተባበር ለኢትዮጱያ የባህል ሙዚቃና መሳሪያዎች በአለም አቀፍ ዘንድ እንዲታወቁ እና እንዲሰሙ የበኩሉን አስተዋፅኦ አድርጎል ።በተለይ በ20 የአሜሪካ ከተሞች ውስጥና በሚታወቁ አዳራሾች እንዲሁም በአገሪቷ በዘመኑ ታዋቂ በነበረው የቴሌቩዥን ዝግጁት ኤክስ ኢሎቮን ላይ የመታየት አድል ነበረው ኦርኬስትራ ኢትዮጱያ ቡድን። በቡድኑ ውስጥም የማንዘነጋቸዉ ቀደምት ስራዎች መካከል ፦ •እኛም አለን ሙዚቃ •አንቺ ልጅ ስምሽ ማነው •ማሚቴና ከቤ •አርብ ለት ማታ ነው ለቅዳሜ አጥቢያ መጥቀስ ይቻላል ። የነዚህ ዜማ ደራሲ ተስፋዬ ለማ ነው። በወቅቱ ቡድኑ ድራማዊ ሙዚቃዎችን ይሰሩ ነበር። በጊዜው በተለይ በኢትዮጱያ በሀገር በቀል መሳሪያዎች በተቀናጀ መልኩ የሚጫወት ቡድን ውስጥ ብቸኛውና በህዝቡ ዘንድ ትልቅ ተቀባይነት ያገኝ እንደነበር ማስተዋል ይቻላል። .ተስፋዬ ከሰራቸው ሌሎች የሚጠቀሰው በአአዩ ባህል ማእከል ውስጥ የመሰረተው እና በግቢው ውስጥ የህብረ ዜማዎች እንዲኖሮ ያደረገ ሰው ነበር ።በተለይ እሰካሁን ድረስ በቲያትር ት/ቤት ውስጥ እየተጠቀሟቸው የሚገኙት ዜማዎች ይጠቀሳሉ ። ጥቂቱን ለማስታወስ ፦ •እንኳን ደስ አላቹ •ጆኒ ምን እዳ ነው •ብቸኝነትን እና ሌሎች ስራዎችን አበርክቶል ለባህል ማእከሉ በሀላፊነት በሰራባቸው ዘመን።

ወደ ቲያትር ቤቱ ህይወት ስናመራ ተስፋዬ ጎልቶ የሚጠቀሰው ራስ ቲያትር ነው። ራስ ቲያትርን ከመርካቶ ሲኒማነት ወደ ቲያትር ቤት ከቀየሩት ግለሰቦች መካካከል አንድ ተስፋዬ ለማ ነዉ። በጊዜውም ቲያትር ቤቱ በህዝቡ ዘንድ ትልቅ ተቀባይነት እንዲሆን አስችሉ እንደነበር በወቅቱ እሱ ስር ያለፉ የኪነ ጥበብ ባለሙያ ሰዎች ይናገራሉ ። ፀሀዬ ዩሀንስ፣ ነዋይ ደበበ ፣ኤልያስ ተባባል ፣ሻምበል በላይነህ ፣አበበች ደራራ ……. ከቲያትር ሰዎች መካከል ደግሞ አዳነች ወ /ገብርኤል፣ ጥላሁን ጉግሳ፣ደብሽ ተመስገን አለምፀሀይ በቀለ ….. ራስ ቲያትር ያፈራቸው እና የጋሽ ተስፋዬ እውቀት ያረፈባቸው የኪነጥበብ ሰዎች ናቸው። ሌላው ለድምፃዊዎቹ በግሉ የዜማ ድርሰቶች ሰርቶል ።ከሰጣቸው ታዋቂ መዚቀኞች መካከል ለጥላሁን ገሰሰ ከሰጠው የሚጠቀሱት ዘንድሮ፣ሶስቱ አልማዝ (ሁለቱ ግጥሞች በጊዜው ሌላ ትርጉም በመሠጠታቸው መታሰሩ ይታወቃል።) አንዳንድ ነገሮች ፣ፍቅርሽ ነው የጎዳኝ ለንዋይ አደል ግመልቱን፣ አይኔ አበባ ለኤፍሬም የሆዴን በሆዴ እና ሌሎች ስራዎችን የሰራ ታላቅ የሙዚቃ ሰው ነበር።

በ1974 /75 አም አከባቢ ቲያትሮች ከቲያትር በመውጣትና በሌሎች ልዩ ልዩ ቦታዎች እንዲታይ ( አጫጭር ቲያትሮችን)እንዲያሰሩ ይፈልግ ነበር ።አናም ፋላጎቱ መገደብ ያልቻለው ተስፋዬ። አምባሳደር አከባቢ አንድ ክለብ መስርቶ ስያሜውን ስቴሪዮ ክለብ(ስክስታ አደራሽ )በማለት ያሰበውን በመስራት እያለ ነበር።በኋላ ላይ ድንገት ክለቡ በእሳት ተቃጣሎ ብዙም ባይዘልቅ ነገር ግን ቲያትርን ከቲያትር ቤት ውጪ በማውጣት ያሰራ ሰው ነበር።

በመጨረሻው የሙዚቃ ህይወት ውስጥ የሰራው ስራ ደግሞ በአብዛኛው የኪነጥበብ ሰው ዘንድ እሰካሁን ድረስ የማይዘነጋው ንቅናቄ ነው ።ህዝብ ለህዝብ ላይ ነበር በወቅቱም የባህል ቡድኑ መሪ በመሆን ስኬታማ ጊዜ አሳልፈዋል ።ነገር ግን ከህዝብ በህዝብ በኋላ በነበረው አገዛዝ ብዙም ደስተኛ ስላልነበሩ በስደት ወደ አሜሪካ አቅንተው እስከ ህይወት ፍፃሜ ድረስም ኖረውበታል። በአሜሪካም ሀገር በነበሩበት ጊዜም የተለያዩ ድርጊቶች በተለይ ቅርስና ውርስ ጋር በተሰየኝ ተቋም ጋር በመተባበር በሙዚቃ ዙሪያ ያሉ ቅርሶችን ሲያሰባስብ ነበር፤ ኑሮን ባረገበት ሰሜን አሜሪካ ። ሌላው በህይወቱ ፍፃሜ አከባቢ ያሰናደው ዳጎስ ያለው መፅሀፍ በማዘጋጀት ለንባብ አቅርቦልናል ።በተለይ መፅሀፎ በኢትዮጱያ ሙዚቃ ታሪክ ከአፄ ሚኒልክ አንስቶ እስከ ደርግ ፍፃሜ ድረስ እንደሚዳስስ ይታወቃል። ሳጠቃልል ይህ ሰው በነበረበት ጊዜ ለሀገረሰብ ሙዚቃና መሳሪያ እንዲሁም ለኢትዮጱያ ሙዚቃ ላበረከተው ነገር ሁሉ ክብር እሰጣለሁ ።በዚህ ዘመን እንደ ተስፋዬ ለማ አይነት ሰዎች ይብዙልን እያልኩ ፅሁፊን አጠናቅቃለሁ።

በዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.