ጥምቀት – ከጃንሜዳ እስከ ጎንደር ያለዉ አንድምታ በጥቂቱ

0
2273
Timket /The Guzo Project
በዳግም ታምሩ
በኢትዮጵያ ከሚከበሩ በአላት ለየት ባለ ስነ ስርአት ከሚከበሩ በአላት ዉስጥ አንዱ ጥምቀት ነዉ። ጥምቀት ከሌሎች በአላት ለየት የሚያደርገዉ ህዝቡ በአሉን የሚያከብረዉ እንደ ሌሎች በአላት በየቤቱ ሳይሆን ታቦቱ በሚያድርበት ስፋራ በመሆኑ በእምነቱ ተከታይና በሆኑና ባልሆኑ ሰዎች በኢትዮጵያ ልዩና ተናፋቂ ያደርገዋል። በአሉ ከመንፈሳዊ ስነ ስርአቱ ባሸገር የተለያየ አድምታ ያለዉ ነዉ።
በጥቂቱ የበአሉን አከባበር በመንፈሳዊ በኩል እንመልከት…
ከተራ – በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ታቦታት ጥር 10 ቀን ከሰዓት በኋላ ወደ ወንዝ ወይም ለጊዜዉ በተሰራ ስፋራ ወርደው ለማረፊያ በተዘጋጀላቸው ቦታ ያድራሉ፡፡ ወደ ስፍራዉም የየአጥቢያው ሕዝብም በነቂስ ወጥቶ ታቦታቱን በማጀብ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ በመሄድ ያገለግላሉ በዕለቱ እዚያው ያድራሉ፡፡ ካህናት ሌሊቱን በማኀሌት ስብሐተ እግዚአብሔር ሲያደርሱ ቆይተው የቅዳሴው ሥነ-ሥርዓት በመንፈቀ ሌሊት ተጀምሮ ከሌሊቱ 9፡00 ሰዓት ይፈጸማል፡፡ ጥምቀት ጥር 11 ቀን ጠዋት በባሕረ ጥምቀቱ ላይ ጸሎት ይደረግና ውኃው ይባረካል፡፡ ሕዝቡም በተባረከው ውኃ ይረጫል፡፡ ከዚህ የሚቀጥለው ታቦታቱን የተሸከሙ ካህናት ከድንኳን ወጥተው ለዝማሬ ማኀሌት በተዘጋጀው አውደ ምሕረት ላይ ይቆማሉ፡፡ መዘምራኑ በዓሉን በተመለከተ ቃለ ማኀሌት በመቃኘት ያሸበሽባሉ፡፡ ከዚያ በወጣት መዘምራን ዝማሬ ጉዞ ወደ ቤተ ክርስቲያን ይሆናል፡፡ በዋዜማው እንደተደረገው ሕዝቡ ሁሉ በቋንቋው፣በባህሉ መሠረት እያሸበሸበ በእልልታና በሆታ በማጀብ ይጓዛል፡ እነዚህ ክንዋኔዎች የራሳቸዉ የሆነ ትርጉም በምሳሌ የተቀመጡ መሆናቸዉን ልብ ልንለዉ ይገባል።  ከላይ የተጠቀሰዉ መንፈሳዊ ክንዋኔዎች ሲካሄዱ ጉን ለጉን የሚደረጉ የበአሉ ገፁታ የሆነ ስነ ስርአቶች አሉ።
Picture by Solomon G/Medhin
Picture by Solomon G/Medhin
16113172_1321293341275423_1471544873158612247_o
Picture by Solomon G/Medhin
በአዲስ አበባ በአሉ በድምቀት ከሚከበርባቸዉ ስፍራዎች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሰዉ ጃንሜዳ ነው። በጃንሜዳ የጥምቀት በአል መነሻዉ ስንመለከት 1933 አም ጀምሮ በአሉ በዚህ ሰፊ ቦታ እንዲከበር ተወስኖ እስኳሁንም እያስተናገደ ይገኛል። የተወሰነበትም ምክንያት ከገነተ ልኡል ቤተ መንግስት የአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አቅራቢ የሚገኝዉ ሰፊ ቦታ ይሄ ስለሆነ ነበር። በወቅቱም ደማቅ እንዲሆን ያረገዉ ንጉሱም፣ ፓትሪያርኩም፣መሳፍንቱም ሆኑ የሀገሪቷ ታላላቅ ሰዎች በስፍራዉ ተገኝተዉ በማክበራቸዉ ነዉ ። በአሉን በማስታከክ ደግሞ የተለያዩ የብሄረሰብ ጭፈራዎች ፣ልዩ ልዩ አዝናኝ ጨዋታዎችና የተለያዩ ነገሮች የሚሸጥበት ቦታ ነዉ።
Picture by Solomon G/Medhin
Picture by Solomon G/Medhin
16143427_1321294331275324_8520524371485519418_o
Picture by Solomon G/Medhin
ሌላዉ ከብሄረሰቡ ጨዋታ ጭፈራ ዉጪ ሊጠቀስ የሚችለዉ ጥምቀት በመጣ ቁጥር የሚጠበቀዉ የታዳጊዎችና የወጣቶች የሀርሞኒካ ጭፈራ ነው። ጭፈራዉ ሴትና ወንድ ሆነዉ የሚጫወቱት ሲሆን ወንዱ ሴቷን ለጭፈራ ጋብዞ የሚያስደስትበተና ከተሳካለት ይዟት የሚሄድበት ጭፈራና ጨዋታ ነዉ። በብሄረሰቦቹም ጨዋታ እንደዚ አይነት ክስተቶች ሊኖሩ የሚችልበት እድል ሰፊ በመሆኑ ከመንፈሳዊ በአልነቱ ባሸገር ወጣቱ የሚገናኝበት ሰፊ በአል ነዉ ጥምቀት። ለዚህም አይደል ስነ ቃሉም እንዲ የሚለዉ “ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ።”  በጥምቀት ጨዋታ ተገናኝተዉ ይዞ እስከ ጋብቻ የደረሱ ሰዎች እንዳሉ በመመልከት የጨዋታዎችን አድምታ እዚ ድረስ መሆኑ መገንዘብ እንችላለን።  ልዩ ልዩ ጨዋታዎችን ለመመልከት ያህል … አይን በጨርቅ ተሸፍኖ እንስራ መስበር፤ የተለያዩ የኳስ ጨዋታዎች፤ በመዘፍዘፊያ ዉስጥ ሳህን ተቀምጦ ሳንቲም ማስቀመጥ እና ሌሎች መሳሰል አስደሳች እና አዝናኝ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ። እንደምሳሌ ጃንሜዳ አልን እንጂ በሌሎች በከተማዉ ቦታዎች በሚገኙ ሜዳዎች በድምቀት የሚከበር በአል ነዉ።
በተጓዳኝም በሀገሪቷ ከሚገኙ ከተሞች በጎንደር በድምቀት የሚገበር በአል ነዉ። በአሉ ከከተራ እስከ ቃና ዘገሊላ ድረስ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በክልሉ ባህልና ትዉፊት መሰረት በድምቀት ከሚከበርበት ከተሞች አንዱ ጎንደር ነዉ። የጥምቀቱ ስነ ስርአት የሚካሄደዉ በፋሲለደስ ገንዳ ዉስጥ ሲሆን ይህን በአል ለመታደም ከተለያዩ አለም ክፍላት ጎብኝዎች በመምጣት ስነ ስርአቱን ይከታተላሉ። እናም ከተማዋ በነዚህ የበአል ቀናት በእንግዶችና በከተማዉ ኗሪ ደምቃ ትዉሏለች። በጎንደር በአሉን ደማቅ እንዲሆን የሚያረገዉ ዋንኛዉ አርባ አራቱም ታቦታት መገኛ ስፋራ በመሆኑ ጭምር ነዉ።
በመጨረሻም ይሄ ኢትዮጵያዊ የሆነዉ በአላችን ከጊዜ ወደጊዜ እንዳይበረዝና የተለየ አድምታ እንዳይኖረዉ ሁሉም የበኩሉን አስተዋፆ በማድረግ ይበልጥ ደማቅ እንዲሆን ማድረግ ተገቢ ነዉ። ሌላዉ ሊበረታታ የሚገባዉ ከቅርብ አመታት ጀምሮ በየሰፈሩ የሚገኙ ወጣቶች ታቦተ ህጉ በሚወጣበትና በሚገባበት ስፈራ የሚያደርጉት ስነ ስርአት ይበል የሚያሰኝ ነዉ በማለት በአሉን ለምታከብሩ በሙሉ መልካም በአል እንዲሆንላቹ በዚህ አጋጣሚ ተመኘን።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.