በዛሬዉ እለት በሰሜን ወሎ በየጁ በምትገኝ ወልዲያ ከተማ በሀገሪቷ ደረጃ እጅግ ዘመናዊ የሆነዉ ስታድየም አስመረቀች

0
1877

በዛሬዉ እለት በሰሜን ወሎ በየጁ በምትገኝ ወልዲያ ከተማ በሀገሪቷ ደረጃ እጅግ ዘመናዊ የሆነዉ ስታድየም እና የስፖርት ማዕከሏን በደማቅ ስነ ስርአት የሀገሪቷ ጠ /ሚኒስተር ሀይለማርያም ደሳለኝና የክልልሉ መስተዳድሮች በተገኙበት እያስመረቀች ትገኛለች ።  በዛሬ እለት የሚመረቀዉ ስታድየም በሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፑ በኩል በሼህ መሀመድ አላሙዲን መልካም ፍቃድ የተገነባ ነዉ ።ግንባታዉ ለአራት አመት የፈጀ ሲሆን ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ በማዉጣት አስገንብተዉ ሙሉ ለሙሉ አጠናቀዋል። .ዘመናዊ ስታድየም ስያሜዉን በሼክ መሀመድ ኣላሙዲን የሚጠራ ሲሆን በወስጡ ያካተታቸዉን የስታድየሙ አካል የሆኑት በጥቂቱ እንመልከት።

ስታድየሙ ሙሉ ለሙሉ የፀሀይና የዝናብ መከላከያ መጠለያ ያለዉ ነዉ።ለየት ያለ የስታድየም ፖዉዛዎች የተገጠመለት። የመሮጫ መሙ በአለም አቀፍ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን መስፈርት ማሟላት የሚችልና የተለያዩ የአትሌቲክስ ዉድድሮችን ማወዳደር የሚችል ነዉ። በቅጥር ግቢ ዉስጥ ደግሞ የመረብ ኳስ፣ የሜዳ ቴኒስ ፣የቅርጫትኳስና የእጅ ኳስ የሚያጫዉቱ ሜዳዎች በተጓዳኝ የያዘ ነዉ።ስፋቱ 25×50 የሆነ ጥልቀቱ ከሁለት እስከ አምስት ሜትር የሚሸፍን የኦሎምፒክ መስፈርት የሚያሟላ የዉሃ መዋኛ ገንዳም ያለዉ ነዉ።ለእንግዶች ማረፊያ የሚሆኑ ክፍሎችም ያሉትና በአንድ ጊዜ አራት ቡድኖች ማስተናገድ የሚችል የተጫዎች መቀየሪያ ያለዉ ነዉ። ደረጃዉን የጠበቀ የድምፁ ማጉያ እንዲሁም በስታድየሙ የሚሰቀሉ የዉጤት ማሳያ የተገጠመለት ና የኢንተርኔት አገልግሎት መጠቀም የሚያስችል ሲስተም የተዘረጋለት ነዉ።ወደ ስምንት የሚሆኑ ዘመናዊ የቴሌቪዥንና የሬድዩ ስርጭቶችን ማስተላለፍ የሚችሎ ክፍሎች ያሉት ነዉ።እና ሌሎች ሊጠቀሱ የሚችሉ ዘመናዊ ስታድየም ሊያሟላቸዉ የሚገባ ነገሮችን ያሟላ ብቸኛዉ ስታድየምና የስፖርት ማዕከል ነዉ። የሼህ መሀመድ ኣላሙዱን ስታድየም በቅርብ ከተገነቡት ስታድየሞች ለየት የሚያደርገዉ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ የተመረቀና በዘመናዊ መልኩ የተሰራ መሆኑ ነዉ።በሀገሪቷም ደረጃ በዘመናዊነቱ የመጀመሪያዉ ስታድየም ያረገዋል። ስታድየሙ 25,155 የመያዝ አቅም ሲኖረዉ በነገዉ እለት የ11 ኛዉን ሳምንት ጨዋታ በማስተናገድ የመጀመሪያዉን ጨዋታ ያረጋል ተብሎ ይጠበቃል።ወልዲያ ከድሬዳዋ ከነማ. በመጨረሻም ሌሎች በመገንበት ላይ ያሉ ስታድየሞች ከዚህ ከወልዲያዉ ስታድየም ብዙ ትምህርትና ልምድ በመዉሰድ የሚሰሩትን ስታድየም ዘመናዊነትን እንዲያላብሱ ማድረግ ይችላሉ እያልን ለመላዉ የኢትዮጱያ ህዝብ እንኳን ደስ አላቹ እንላለን።

በዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.