ብቸኛዉን የኢትዮጱያ የአፍሪቃ ዋንጫ በትዉስታ

0
948

በአፍሪካ ከሚደሩጉ የስፖርት ዉድድሮች ዉስጥ ግንባር ቀደም ቦታ የሚይዘዉ የአህጉሪቱ የእግር ኳስ ዉድድር ነዉ።ጅማሮን ካደረከበት እኤአ 1957 ዉድድሮ ከሱዳን ተነስቶ ቅዳሜ እስከ ሚጀምረዉ የጋቦኑ የ2017 አፍሪቃ ዋንጫ ደርሶል። በነዚህ አመታት ሀገራችን ኢትዮጱያ በተሳትፎ ደረጃ ለ10 ጊዚያት ተሳትፋለች አብዛኛዉን ማለት 95 እጅ የሚሆነዉ የዉድድሮ የመጀመሪያ አመታት ዉስጥ የተሳተፈችበት ነዉ። ሌላዉ ሶስተኛዉን ፣6 ተኛዉን እንዲሁም 10 ኛዉን የአፍሪቃ ዋንጫ አስተናግዳለች። ከዚሁ ሁሉ ተሳትፎ ኢትዮጱያ አንድ የአፍሪካ ዋንጫ በልታለች ።ራሷ ባስተናገደችዉ ሶስተኛዉ አፍሪቃ ዋንጫ የድሉ ባለቤት ነበረች ።እናም ለዛሬ ሰፊዉን ነገር ለዚህ ዋንጫ በመስጠት የነበረዉን ነገር ለማስታወስ እንሞክራለን።

15977034_1315692965168794_1801029623856636873_n

በሶስተኛዉ አፍሪቃ ስለነበረዉ ነገር ጥቂት እንበላቹ። በመጀመሪያ ዉድድር ኢንዲጀመር ካደረጉት ሀገራት ሁለቱ ሱዳንና ግብፅ በሀገራቸዉ አንደኛዉን ና ሁለተኛ ሲያዘጋጅ በቀጣይ ባለተራ የነበረችዉ ኢትዮጱያ ነበረች ። ለኢትዮጱያ በወቅቱ ትልቅ ዉድድር ስታስተናግድ በተለይ በስፖርቱ ይሄ የአፍሪቃ ዋንጫ የመጀመሪያዉ ነዉ። በጊዜዉ 1961 እኤአ ነበር ዉድድሮ እንዲደረግ የታሰበዉ ነገር ግን በወቅቱ በሀገሪቱ ዉስጥ በተከሰተዉ የታህሳሱ ግርግር ምክንያት ለወራት ገፋ በማለቱ ወደ 1962 ተሻግሮ ሊካሄድ ችላል ።  በዉድድር የተሳተፉት ሀገራት ግብፅና ኢትዮጱያ በቀጥታ ሲያልፎ ፤ግብፅ ከ1962 በፊት በተደረገዉ ዉድድር አሸናፊ በመሆኖ ስታልፍ ኢትዮጱያ አዘጋጅ ሀገር በመሆን ነበር በዉድድሮ ዉስጥ የገባቸዉ።ሌሎች 7 አገሮች ደግሞ ማጣሪያ አድርገዉ ሁለት ሀገራት አሳልፈዋል፤ቱኒዚያና ዩጋንዳ ነበሩ ።

15977194_1315692821835475_3774031838102095985_n 15977230_1315693138502110_5766778844869748348_n

ኢትዮጱያ የመጀመሪያ ጨዋታዋን ከቱኒዚያ ጋር ነበር የተጋጠመችዉ ።በጨዋታዉም ቱኒዚያ ቀድማ ሁለት አግብተን እረፍት የወጡ ቢሆን የማታ የማታ ከኋላ ተነስቶ የኢትዮጱያ ቡድን ሁለትግቦች በማግባት ለተጨማሪ ሰአት ደረሰ ።በተጨማሪ ሰአትም ሁለት ግቦች በማግባት በአጠቃላይ አራት ለሁለት በማሸነፍ ለፍፃሜ ደረሰን ከግብፁ ቡድን ጋር በግብፅ በኩል ደግሞ ዩጋንዳን ሁለት በማሸነፍ ነበር የደረሱት። ከፍፃሜዉ በፊት የነበሩ ነገሮች በ2 ተኛዉ አፍሪቃ ዋንጫ አዘጋጅ የነበረችዉ ግብፅ ነበረች። እናም በነበራቸዉ ጨዋታ 4 ለ0 ተሸንፎ ነበር የኢትዮጱያ ቡድን። ኢትዮጱያ በጊዜዉም ወደ ዉድድሮ ሲያቀኑ ጫማቸዉን ግብፅ ዉስጥ አሰፍተዉ ነዉ ወደ ዉድድር የገቡት ።ነገር ግን ጫማ ሰፊዉ በአግባቡ ባለ መስራቱ ጉጡ እየተነቀለ በባዶ ተጫዉተዉ ነዉ ጨዋታዉን የተሸነፎት ። በነገራችን ላይ ጫማዉ ቼርቪኮ የሚባል ሲሆን በጎማና በእንጨት እንዲሁም በሚስማር የሚሰራ ነበር።የሚያሰራበት ቦታም ፒያሳ በሚገኝ ጌታሁን ቤት ዉስጥ ነበር። በኢትዮጱያ በኩል የዛን ጊዜ የተሰራባቸዉን ደባ ለመካስ የተዘጋጅ ይመስላሉ።ግብፆች የዉድድሮን የበላይነታቸዉ ማስቀጠል ይፈልጋሉ።በወቅቱ ግብፅ የተሻለ የእግር ኳስ እድገት ነበራት። . ጨዋታዉ በቀኃሥ ስታድየም ነዉ የሚደረገዉ ጃንሆይም በቦታቸዉ ተገኝተዋል ።ጨዋታዉ ተጀመረ ግብፆች ቀዳሚ የሆኑበትን ጎል አገቡ ። እረፍት በግብፆች የበላይነት ተጠናቀቀ ።በሁለተኛዉ አጋማሽ የተወሰነ የደከሙት ግብፆች ጨዋታዉ ሊያልቅ 15 ደቂቃ ሲቀረዉ ኢትዮጱያ የአቻ ነቱን ግብ በተክሌ አማካኝነት አስቆጠረች ነገር ግን ህዝብም ሆነ ተጫዎቹ ደስታቸዉን ሳያጣጥሙ ወዲያዉ ግብፆች አስቆጠሩና ዉጥረቱ የባሰ አዘለ ።በተደጋጋሚ ወደ ግብፅ ሜዳ እየደረሱ ኢትዮጱያ ቡድን ጨዋታዉን ለማሸነፍ እየጣረ ነዉ። ጨዋታዉ ሊጠናቀቀ 2 ደቂቃ ሲቀረዉ በሚደንቅ ሁኔታ በጠበበ አንግል ሎቻኖ ቫሳሎ አገባ ።ህዝቡ ሎቾ ሎቾ ብሎ ጨፈረ ። ተጨማሪ ሰአት ተጨምሮ የሀይል ሚዛኖ ወደ ኢትዮጱያ በመምጣት የሎቻኖ ታናሽ ወንድም ኢታሎ ከርቀት በመምታ ግባዉን አስቆጠረ ።ማስተማመኛ ግብ የፈለገዉ መንግስቱ ከመሀል ሜዳ የግብፅ ተጫዎችና ግብ ጠባቂዉ በማለፍ ኳሱንም ራሱን ወደ መረቡ ዉስጥ ከቶ ጨዎታዉ 4 ለ2 በሆነ ዉጤት በማለቅ የሶስተኛዉ አፍሪቃ ዋንጫ ባለቤት ሆኑ።ከንጉሱም እጅ አምበሉ ሎቻኖ ዋንጫዉን ተቀበለ።

16003096_1315693318502092_5020695874051043552_n

የባለፈዉን የአፍሪቃ ዋንጫ የነበረዉን ዉጤት በዚኛዉ ዋንጫ በቀላቸዉን በማሸነፍ ተወጡ። በይድነቃቸዉ ተሰማ የአሰልጣኝነት እየተመራ ያገኘነዉ የሶስተኛ አፍሪካ ዋንጫ ብቸኛዉ የአፍሪቃ ዋንጫችን ነዉ። በዉድድሮ መንግስቱ ወርቁ ኮከብ ተጫዎችና በሶስት ግብ ኮከብ ግብ አግቢ በመሆን ለኢትዮጱያ ለራሱም ሌላ ድል አምጥቷል ።  ከዚህ ጊዜ በኋላ ከተሳተፊነት በዘለለ የተሻለ ዉጤት ማምጣት አልቻልም።መስራች በነበርንበት እግር ኳስ ተወዳዳሪ እንዲሁም ተፎካካሪ መሆን ሲገባን በአንፃሩ ለመሳተፎ 31 አመት ጠብቀን።

ሌላዉ አይረሴዉ የአፍሪቃ ዋንጫ ትዝታ ከረጅም ጊዜ በኋላ (ከ31 አመታት መሆኑ ነዉ።)ያለፍንበት የ2013 የደ/ አፍሪቃ የአፍሪቃ ዋንጫ ነዉ ።በሁለት ጨዋታ ወደ አፍሪቃ ዋንጫ ቢያልፍ ቡድኑ በህዝቡ ዘንድ የሚዘነጋ ጊዜ አልነበረም። በተለይ የመጨረሻዉ የአአ ስታድየም የሱዳኑ ጨዋታ ።ተመልካቹ ከአንድ ቀን በፊት ነዉ ስታድየም ተገኝቶ በማደር የገባዉ።በወቅቱ በየትኛዉም አቅጣጫ የሚወራዉ ስለ ኢትዮጱያ ብሄራዊ ቡድን ነበር ።ነገር ግን በሰዉነት ቢሻዉ የሚመራዉ ቡድን የመጀመሪያዉ ደረጃ ቢያሳካም በዉድድሮ ላይ የሚጠበቀዉን ያህል ዉጤት ይዞ ሳይመጣ የመጨረሻ ደረጃ ይዞ መቷል።  በመጨረሻም ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻዉ ዘመን በኢትዮጱያ ብሄራዊ ቡድን በኩል የተሳተፎሙ ዋንጫም ላስበሉን የቡድኑ አባላት ድረገፃች በዚህ አጋጣሚ ክብር መስጠት ትወዳለች እያልን ፅሁፋችን በዚህ እናጠቃልላለን።

በ ዳግም  ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.