ገናን በኢትዮጱያ እና ኢትዮጵያዊ በሆኑ ክንዉኖች

0
956

በሀገራችን በገና በአል ወቅት የሚደረጉ የተለያዩ ክንዉኖች አሉ ።እናም እዚህ ድርጊቶች መቼታቸዉ የተለያየ ቢሆንም ለበአሉ የሚሰጡት ትርጉም ግን አንዱ ነዉ።ከነዚህ መሀል ሁለቱኑ በጥቂቱ እንመለከታለን ፤የገና ጨዋታና የላልይበላ የገና አከባበር።

የገና በአል ዋና አላማ የእየሱስ ክርስቶስ በቤተልሄም በግርግም ዉስጥ መወለድን በማብሰር የልደት በአሉ ይከበራል ።

በአሉን በኢትዮጱያ በተለይ በቀደምት ጊዜ ከሚያደምቁት ክኖቶች ዉስጥ አንዱ የባህል ጨዋታ አለ የገና ጨዋታ ይሰኛል ።የጨዋታዉ መነሻ አባቶች በአፈ ታሪክ እንደሚያወሩት ከሆነ ክርስቶስ መወለዱን የሰሙ እረኞች ተደስተዉ በጊዜዉ የተጫወቱ ጨዋታ ይሄ አሁን የገና ጨዋታ የምንለዉ ነበር።እናም ከዛን ጊዜ ጀምሮ ልደቱ በሚከበረብት ጊዜ እነዚህ እረኞች በየአመቱ ይጫወቱ እንደነበር ታሪክ ይናገራል ። ይሄ ታሪካዊ ጨዋታ በኢትዮጱያዊያን ነገስታት ዘመን ይጫወቱ የነበረ መሆኑ የቀደምት ድርሳና ይተነትናሉ።እንዲያዉ ብዙ ጊዜ ገና ሲመጣ በአፄ ሚኒልክ ዘመን ይጫወቱ የነበረዉን የገና ጨዋታ ሲታወስ እንሰማለን ።ከቤተመንግስቱ ሁለት ቡድኖች ተወክለዉ ወደ ሜዳ በማቅናት የሞት ሽረት ትግል ያረጉ እንደነበር የሚታወስ ነዉ። ሁለቱ ቡድኖች አንደኛዉ የ የአፄ ሚኒልክ ሲሆን አንደኛዉ ደግሞ የእቴጌ ጣይቱ ነበሩ ።አንዱ ካንድ ላለመሸነፍ በሚደረግ ጥረት ዉስጥ የተለያየ ስልቶች ይጠቀማሉ። በተለይ በወቅቱ ይባሉ ከነበሩ ዜማዎች ለማስታወስ የእቴጌ ቡድን አሸናፊ ከሆነ .

እጅ የለዉም ወይ እእጅ የለዉ ወይ

የሚኒልክ ቡድን እጅ የለዉም ወይ

ሌላዉ ገና ሲመጣ የማይረሳዉ ዜማ አለ በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ

በገና ጨዋታ

የለም ሉሌ ጌታ የነዚህ ስንኞች ትርጉም ዝም ብለን በግርድፋ ብንመለከተዉ በሁሉም ሰዉ ዘንድ ጨዋታ የምትጫወተዉ ጨዋታ መሆኑ ይነግራል ።

እስከ ጃንሆዬ ዘመን ድረስ ይሄን ጨዋታ በቤተመንግስት ስርአት በኩል ይጫወቱ ነበር።በነገራችን ላይ ጨዋታዉ በየክልሉ የተለያየ ስያሜ ተሰጥቶ የሚካሄድ የባህል ስፖርት ነዉ።

ነገር ግን በአሁኑ ሰአት ጨዋታዎች የሚካሄድ ሲሆን ነገር ግን ተቀባይነቱ ከፈረንጅ የገና በአል አከባበር ያነሰ ቦታ ነዉ የሚሰጠዉ በሀገራችን ህዝብ ዘንድ። ይሄን የመሰለ ታሪካዊ የሆነ እና የራሳችን መገለጫ የሆነዉን ጨዋታ ብዙም እዉቅናና አለመሰጠቱ ይበልጥ ያናድዳል።በቀደመዉ ወቅት ለገና በአል የሚሰጠዉ ነገር የጎላ እንደነበር መገንዘብ ቀላል ነዉ።

ሌላዉ የገና በአል ሲመጣ የማይዘነጋዉ በአሉ በድምቀትና በተለያዩ መንፈሳዊ ድርጊቶች የሚከናወንበት አንድ ታላቅና ታሪካዊ ስፋራ አለ ።ላልይብላ ይሰኛል ፤በዚህ ታላቅ ስፋራ ላይ በአሉ ድርብ ነዉ። ከክርስቶስ ልደት ቀን እኩል የተወለደዉ ንጉስ ላልይብላ ልደትም በዚሁ ቀን ይከበራል።በመሆኑም የገና በአል ላልይብላ ላይ በመንፈሳዊ በኩል ከሌላዉ ለየት እንዲል ያረገዋል ።በበአሉ ወቅትም የተለመዱት የቤተ ክርስትያን ስርአቶች በድምቀት የሚካሄድ (የቅዳሴ ፣የማህሌት እንዲሁም የቅኔ ስርአቶችን ያጠቃልላል) ሲሆን ነገር ግን በዚህ ቦታ ብቻ የሚከናወንና በአሉን ይበልጥ ደማቅ የሚያረገዉ ቤዛ ለኩሉ የሚባለዉ የቀለም አይነት ነዉ።የዚህ ቀለም ስርአት በአጭሩ ለማየት እንሞክራለን።

12፡00 ሰዓት ጀምሮ ጥንግ ድርብ፣ ካባ እንዲሁም ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናት ከአስራ አንዱ ቤተመቅደስ ከእያንዳንዳቸው ከአስራ ሁለት ያላነሱ ካህናት ይህንን ያሬዳዊ ዜማ ለማጀብ ወደ ማሜ ጋራ /ቤዛ ኩሉ ዓለም ሥነ ሥርዓት የሚካሄድበት ቦታ/ ይወጣሉ።ከዛ በመቀጠል ልክ አንድ ሰዓት ሲሆን ከላይና ከታች የሚሰለፉ ካህናት ቦታቸውን ይይዙና እስከ 4 ሰዓት በሚፈጅ ክንውን እየተቀባበሉ ለሀገር፣ ለወገን፣ ለምድር ሰላም በረከት የሚጸለይበት ክንዋኔ ነዉ ፤ቤዛ ለኩሉ ዓለም። ይሄን ስርአትና ክንሁን ለመመልከት በሀገር ዉስጥ ከተለያየ ቦታ የሚገኘ ህዝቦች በስፋት ይታደሙበታል።እንዲሁም የዉጪ ሀገር ዜጋ የሆኑ ሰዎችም እንደቱሪስት መስህብነት ከሚመለከቱት ድርጊት ከሚጠቀሱት አንዱ ይሄ ክንዉን ነዉ።

በመጨረሻም ማለት የምንፈልገዉ ለአዲሱ ትዉልድ የገና በአል በራሳችን መንገድ ማክበር የምንችልበትን መንገድ የምናሳዉቅበት ጊዜ መምጣት ያለበት ይመስለኛል ።በተለይ የፈረንጆችን ብቻ እያከበረን የራሳችን የሆኑት ጨዋታዎች ሆነ መንፈሳዊ እሴቶች መዘንጋት የለበትም።በተለይ የኢትዮጱያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ከህብረተሰቡ ጋር ተባብር ትልቅ የማሳወቅና የማስተማር ስራ መስራት አለባት እያለን ድረ ገፃችን በአሉን ለሚያከብሩ በሙሉ መልካም የገና በአል ይሁንላቹ እያልን መልካም ምኞታችን እንገልፃለን።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.