የዘጠኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሳምንቱ አጋማሽ ይቀጥላሉ

0
800

በዘንድሮ የዉድድር አመት ጨዋታዎች በስራ ቀን ሲደረጉ ይሄ የመጀመሪያዉ ሳምንት ያረገዋል ።የእረፍት ቀናት የገና በአል በመዋሉ ምክንያት ጨዋታዎች ረእቡ፣ ሀሙስና አርብ ይደረጋሉ። አዲስ አበባ ላይ በሁለቱ ቀናት የሊጉን ግማሽ ጨዋታዎች ያስተናግዳል። ዛሬ ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት ሲል ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሊጉ ከሳምንት ወደ ሳምንት የተሻላ የመጣዉን መከላከያ ጋር ይጫወታል።ባለፋት ሳምንት ከመመራት ተነስቱ ያሸነፈዉ መከላከያ ወጥ አቋም ማሳየት ያቃተዉ ባንክ ጨዋታዉ ሊከብደዉ ይችላል። 11:30 ሲል ደግሞ ሁለቱ በዘንድሮ አመት ወደ ሊጉ የተቀላቀሉትን ክለቦች ያገናኘል። አአ ከነማ ከፋሲል ከነማ ።ዘንድሮ ከተቀላቀሉት ክለቦች የተሻለ ነጥብና አቋም ያለዉ ፋሲል ከነማ ሲሆን በአንፃሩ ደካማ ዉጤት ከሰበሰበዉ ክለብ አንዱ የስዩም ከበደ አአ ከነማ ነዉ።ፋሲል ወደ ሊጉ ተፎካካሪት ለመጠጋትና አአ ከነማ በበኩል ከወረጅ ቀጠና ለማድረግ የሚጫወቱት ተጠባቂ የምሽቱ እና የዛሬ የመጨረሻ ጨዋታ ነዉ። የክልል ጨዋታዎች ሀሙስና አርብ የሚካሄድ ናቸዉ ።የሀሙስ ጨዋታዎች . የሊጉ ሰንጠረዥ ግርጌ ላይ የሚገኘዉ ሀዋሳ ከነማ በከተማዉ ወላይታ ዲቻን ያስተናግዳል።

በዘንድሮ የዉድድር አመት የተጠበቀዉን ዉጤት ማግኘት ያልቸዉ ሀዋሳ ከነማ የሀሙሱ ጨዋታ ከዚህ የደረጃ ለመዉጣት የግድ ማሸነፍ ይጠበቅበታል።በወላይታ ዲቻ በኩል በሊጉ መሀል ሰፋሪ ቦታ የተቀመጠ ቢሆንም ነገርግን የዛሬዉ ጨዋታ አሸንፎ ወደ ሊጉ አናት ለመጠጋት ያለዉን እድል የሚያሰፋ ይሆናል። ጅማ ላይ ሌላዉ የሚጠበቅ ጨዋታ ሁለቱ በቡና ሴክተሩ ድጋፍ የሚደረግላቸዉ የክልል ክለቦችን ያገናኛል። ጅማ አባቡና ከሲዳማ ቡና ።ሲዳማ በደረጃዉ የሊጉ አናት የተቀመጠ ሲሆን በበኩሉ ጅማ ከሊጉ የመጨረሻ ተርታ ላይ ተቀምጦ ነዉ። የነገዉን ጨዋታ የሚጠብቁት።የሊጉ መሪ አርባምንጭ ተገኘቷል ።ደደቢት ከ አርባምንጭ ከነማ ።ደደቢቶች ከቴክኒክ ዳሬክተሩ እየተመራ ያለመሸነፍ ጉዞን አስቀጥሎ በነገዉ እለት አርባምንጭን ይገጥማል ።አዞዎቹ እንደ መከላከያ ሁሉ ከሳምንት ወደ ሳምንት የተሻለ ነጥብ ይዘዉ በመምጣት በሰንጠረዥ አጋማሽ ላይ ተቀምጠዋል።በሳምንቱ ከሚጠበቁ ጨዋታዎች ዉስጥም አንድ ደደቢት አሁንም የሊጉ መሪነቱ ለማስጠበቅ አርባምንጭ ላይ የተሻለ ነጥብ ይዞ መምጣት ይጠበቅበታል።

አአ ላይ ደግሞ የዉጤት ቀዉስ ዉስጥ የሚገኘዉ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ኣዳማ ከነማን ዘጠኝ ሰአት ሲል ያስተናግዳል።ኣዳማዎች በዘንድሮ የሊጉ ግስጋሴ ስኬታማ ጊዚያት እያሳለፈ የሚገኘ ክለብ ነዉ ።ከሜዳ ዉጪ በተጫወታቸዉ ጨዋታዎች የተሻለ ነጥብ ይዞ የሚገኝ ክለብ ነዉ። ምሽት 11:30 ሲል የአአ ክለብ የምስራቁን ክለብ ያስተናግዳል ።ቅ/ጊዮርጊስ ከድሬዳዋ ከነማ ።በደጋፊዉ ዘንድ ከደርቢዉ ጨዋታ በኋላ ብዙ ተቋዎሞችን ያስተናገደዉ ጊዮርጊስ በጥሩ ጨዋታ ተጫዉቶ ወደ አሸናፊነት ይመለሳል ተብሎ ይጠበቃል።በድሬዳዋ በኩል በአማካኝ በጨዋታ 1 ነጥብ እያገኘ በአብዛኛዉ በመከላከል የሚወጣ ቡድን ነዉ የነገዉ ን ጨዋታ ከጊዮርጊስ ላይ የተሻለ ነጥብ ይዞ ወቶ በሊጉ ለመቆየት ይረዳዋል ተብሎ ይጠበቃል። ሌላዉ በእለተ አርብ የሚደረግ ብቸኛዉ ጨዋታ መልከ ቆሌ ላይ ወልዲያ ከነማ ከየኢትዮጱያ ቡና ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ነዉ።በኢትዮጱያ ቡና በኩል ሁለተኛዉ የክልል ጨዋታ ነዉ ወደ መልከ ቆሌ ሲያቀና ።በከተማ ደርቢ ወደ ማሸነፍ ሂደቱ የገባዉ ቡድኑ ወደ ዋንጫ ፋክክክር ለመግባት የአርቡን ጨዋታ ላይ ጥሩ ዉጤት ይዞ መመለስ አለበት።በወልዲያ በኩል በቡና ካሸነፈ ነጥቡን ከቡና እኩል አርጎ ለጊዜዉ ቢሆን ከወራጅ ነፃ ለመዉጣት የተሻላ አማራጭ ይኖረዋል ። በመጨረሻም ለመላዉ የክርስተና እምነት ተከታዮች መልካም የገና በአል እንዲሆን በድረገፃችን በኩል እንገልፃለን።

በ ዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.