የሀገሪቷ ትልቁ ጨዋታ በኢትዮጱያ ቡና አሸናፊነት ተጠናቀቀ::

0
874

የ8 ተኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች ቅዳሜና እሁድ የተካሄዱ ሲሆን ቅዳሜ 7 ጨዋታዎች በየክልሉና መስተዳደር ከተሞች ተከናዉነዋል። አንድ ቀሪ ጨዋታ ደግሞ በእለተ እሁድ አአ ላይ ተካሄዶል። የቅዳሜ ጨዋታዎች አአ ላይ በዘጠኝ ሰአት ደደቢት ከኢትዮጱያ ንግድ ባንክ ሲያገናኝ። አሞራዎቹ ባለ ድል ሆነዋል 2 ለ1 በሆነ ዉጤት ።በዚህ ጨዎታ የሊጉ ኮከብ አግቢ ጌታነህ ከበደ ሁለቱንም ግቦች በማሳረፈ በ 8 ጎል እየመራ ይገኛል። የሊጉ መሪነትም ከጊዮርጊስ የተቀበለበት ዉጤትም ሆኖ ተመዝግቧል።

15841058_1303965889674835_2095671956_n

ጎንደር ፋሲለደስ ስታድየም ላይ የሄደዉ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ያለግብ አቻ ተለያይቶ መቷል ።በሊጉ ብቸኛዉ አቻ ዉጤት የተጠናቀቀ ጨዋታ ሆኖ ተመዝግቦል ።በወረጅ ቀጠና ያለሁን ጉዞ ቀጥላል ኤልፓ ። ኣዳማ አበበ ቢቂላ ላይ የተጓዘዉ ጅማ አባቡና ተሸንፎል ።1 ለ0 በሆነ ዉጤት የአሸናፊ ከበደ ቡድን አሁንም አልሸነፍ ባይነቱን ቀጥሎ የሊጉ የመጀመሪያ ተርታ ላይ ተቀምጧል። በወንድሟሟች ደርቢ ይርጋለም ላይ ሲዳማን ከሀዋሳ ያስተናገደዉ ጨዋታ። የሳምንቱ ከፍተኛ ግብ የተቆጠረበት ጨዋታ ሆኖ ተጠናቋል ።የድሉ ባለቤትም ሲዳማ 3 ለ1ዉጤት አሸንፎል።በሊጉ አናት የነበረዉን ነጥብም አስቀጥሏል።በሊጉ ግርጌ ላይ የሚገኙት ሀዋሳዎች ከዚህ ለመዉጣት የከበዳቸዉ ይመስለኛል። በቅርቡ ስታድየሙን ጨርሶ ያጠናቀቀዉ ወልዲያ ከነማ ወደ ሶዶ አቅንቱ 1 ለ0 በሆነ ዉጤት ተሸንፎ መቷል ።አዲስ መጪዎቹ ወጥ አቋማቸዉን በሊጉ ማሳየት ያቃታቸዉ መሰለኝ። በሊጉ ከፍተኛ የደሞዝ ክፍያ የሚያወጣዉ አርባምንጭ ወደ ምስራቅ አቅንቱ ከድሬዳዋ ላይ ሶስት ነጥብ ማግኘት ችላል። ሌላዉ የቅዳሜ እለት የመጨረሻ ጨዋታ የነበረዉ መከላከያ ከአዲስ አበባ ከነማ ያደረጉት የ11:30 ጨዋታ ነበር።በጨዋታዉ እንደባለፈዉ ሳምንት ሁሏ ከመመራት ተነስቷ መከላከያ 2 ለ1 በሆነ ዉጤት ባለ ድል ሆናል።በአዲስ አበባ ከነማ በኩል እንደ በፊተኞቹ ሳምንታት አስጠብቆ መዉጣት አልቻለም ።በጨዋታ ሌላዉ አስገራሚ ነገር የሊጉ ፈጣን ጎል መመዝገቡ ነዉ ፤በ28 ተኛዉ ሰከንድ የአአ ከነማ አጥቂ ሀይሌ እሸቱ ነበር ያስቆጠራት።

የእሁዱ ጨዋታ በእለተ እሁድ የተካሄደዉ ብቸኛዉ ጨዋታ የሀገሪቱ ትልቁ ተጠባቂ ጨዋታ ነበር ። ወደ ስታድየም ለመግባት የእግር ኳስ ተመልኳቹና ደጋፊዉ ከጠዋቱ 1 ሰአት ጀምሮ በስታዲየሞች አከባቢ በመገኙት ነበር ፤የስታድየም መግቢያ ሰአት ሲጠበቅ የነበረዉ ። ይከፈታል ከተባለበት ሰአትም ቀድሞ የስታድየም በሮች ተከፋቱ 6:20 ላይ። ተመልካቹም ፍፁም ስፖርታዊ ጨዋነት በተላበሰ መልኩ ወደ ስታድየም በመግባት የሚወዱትን ክለብ ሲያበረታታ ነበር ።የጨዋታዉ ሰአት እንደደረሰም የቀዘቀዘ የሚመስለዉ የደጋፊዎች ድምፅ ኢትዮጱያ ቡና ሲያገባ ዳግም ተነሳ ።የተሻለ የኳስ ቁጥር የነበረዉ ቡና በተለይ 15 ደቂቃ እስከ 35 ደቂቃ ድረስ የዘለቀ ነበር ።ከእረፍት መልስ የአጨዋወት ስልት የቀየር የመሰለዉ ቅ ጊዮርጊስ የተሻለ የመሰለ እንቅስቃሴዎች ለማድረግ ሙከራ አድርጎል ።

ሌላዉ ኢት.ቡና በበኩሉ ወደ ኋላ በማፈግፈግ በጨዋታ ሶስት ነጥብ ይዞ ለመዉጦት ያደረገዉ የጨዋታ እንቅስቃሴ አሳክቶ ወቷል ።በተለይ የቡና ተጫዎቹ የጊዮርጊስን የማጥቃት ዘመቻን ለመግታት ሰአቱኑ በመግደል ያሰቡትን ይዘዉ ሄደዉ ከወራጅ ቀጠና መዉጦት ችለዋል። . . በሁለቱም ክለብ በኩል ግን ተመልካችን ያስደስተ ጨዋታ አላየንም ነገር ግን በስፖርታዊ ጨዋነት በኩል ከምንገዜዉም የተሻለ ድርጊት በስታድየሙ ዉስጥ ተመልክተናል ።እናም በሁሉም ጨዋታዎችይሄ ነገር እንዲቀጥል ተመኘን። . . ሊጉንሁለት ክለቦች በእኩል 17 ነጥብ ይመሩታል በግብ ክፍያ ተበላልጠዉ።በተከታታይ ሲቀመጡ ደደቢት ና አዳማ በሶስተኝነትም የተቀመጠዉ ጊዮርጊስ ሌሎቹን አስከትሎ ከሲዳማና ከመከላከያ ጋር በእኩል 14 ነጥብ ተቀምጦል። በሊጉ ግርጌ ደግሞ ሶስት ክለቦች በእኩል አምስት ነጥብ በግብ ክፋያ ተበላልጠዉ ተቀምጠዋል ።በተርታ ከ14 ተኛ እስከ 16 ተኛ ፤አአ ከነማ ኢትዮ ኤሌክትሪክና ሀዋሳ ከነማ ናቸዉ።

በ ዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.