በሀገራችን እግር ኳስ ተጠባቂዉና ግንባር ቀደም ጨዋታ የኢትዮጱያ ቡና ከቅ/ ጊዮርጊስ

0
885

በዳግም ታምሩ

በኢትዮጱያ እግር ኳስ ዉስጥ ትልቅ ቦታ ከሚሰጣቸዉ ጨዋታዎች ዉስጥ አንድ በአዲስአበባ ከተማ ዉስጥ የሚገኙትን ክለቦች የሚያገናኙዉ ይጠቀሰላል። የኢትዮጱያ ቡና ከቅ/ጊዮርጊስ በዘንድሮ የኢትዮጱያ ፕሪሚየም ሊግ ሁለቱ የከተማዉ ክለቦች በ8 ተኛዉ ሳምንት የፊታችን እሁድ በ10 ሰአት በአአ ስታድየም ይገናኛሉ።በ2009 አም የመጀመሪያ የእርስ በእርስ ጨዋታቸዉ ነዉ።

giorgis

ሁሌም በስፖርት ቤተሰቡ ሆነ እግር ኳስን በሆነ አጋጣሚ ለመመልከት ከሚመረጡ ጨዋታዎች ዉስጥ አንዱ ነዉ። ሁለቱ ክለቦች በየትኛዉ የነጥብ ደረጃ ቢቀመጡም የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነዉ።ለምሳሌ የዘንድሮን የሊጉ የነጥብ ደረጃዎችን መመልከት በቂ ነዉ።በ 14 ነጥብ የሊጉ አናት የሚገኙዉ ጊዮርጊስ ሲሆን በሰንጠረዥ የመጨረሻ ደረጃዎች 12 ተኛ ላይ ተቀምጦ በ7 ነጥብ ይዞ የሚገኙዉ ቡና ነዉ ።እንደዚህ ተለያይተዉ ግን ተጣባቂነቱን አይቀንስም።

ደርቢዉ የተለያዩ ስያሜ በተለያየ ጊዜ ሲሰጠዉ አስተዉለናል ፤የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል ። ሸገር ደርቢ ፊንፊኔ ደርቢ የአዲስ አበባ ከተማ ደርቢ የሚሉት ይጠቀሳሉ ።

እንደ ደርቢዉ ስያሜ ሁሏ የክለቦቹም ስያሜ እንደ ወቅቱ ሁኔታና ጊዜ ተለዋውጠዋል ። የአሁኑ የኢትዮጱያ ቡና የሚለዉ ስያሜ ከማግኙቱ በፊት ንጋት ኮከብ ከዛም ቡና ገበያ በሚል ስያሜዎች ተጠቅሟል። በቅ/ጊዮርጊስ በኩል ደግሞ መነሻዉ ላይ ቅ/ጊዮርጊስ ሲባል በመሀል አዲስ ቢራ የሚለዉን ስያሜ ይጠቀም ነበር ።

1

 

የደጋፊዎቹ ተፆኖ በደርቢዉ በእድሜ ትልቁ የሆነዉ ጊዮርጊስ ክለብ እንደ ቀደምትነቱ የብዙ ደጋፊ ባለቤት ነዉ ።ነገር ግን ባለፉት አመታት እየቀነሰ የመጣ የነበረዉ የደጋፊ ቁጥር በቅርብ ጊዚያት ዳግም እጨመረ መምጣቱን ማስተዋል ቀላል ነዉ ።በዘንድሮ የሊጉ አጀማመር የደጋፊ አጨፋፈር ስልት ከምንግዜዉ የተለየ የአደጋገፍ ስርአት ይዞ የመጣ ነዉ።

የኢትዮጱያ ቡና በኩል ደግሞ ምስረታዉ ከ ጊዮርጊስ በኋላ ቢሆንም ከ80 ዎቹ መጨረሻ ጀምሮ የደጋፊ ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ መቷል ።በተለይ ዉጤቱ ደጋፊዉ በሚፈልገዉ ደረጃ ክለቡ ባላመጣባቸዉ ጊዚያትም ከጉኑ በመቆም ለክለቡ በህብረት ድጋፍ በማድረግ የስታድየም ድምቀት ናቸዉ።በዘንድሮ አመት ትንሽ የተቀዛቀዘ የሚመስለዉ የደጋፊዉ ሁኔታ በሊጉ የ7 ተኛ ሳምንት ጨዋታዎች መንሰራራት እንደጀመረ አስተዉለናል። ሌላዉ የሁለቱ ክለብ ደጋፊዎች ከምንም በላይ ለጨዋታዉ ደምቀት እንዲኖረዉ ትልቁን ቦታ ይይዛሉ። የነሱ በሰላማዊና በሰከነ መልኩ መደገፍ የላቀ ድርሻ አለዉ።በተለይ በሁለቱ ጨዋታ ቀን ስታድየም ገብቶ የማያዉቅ ግለሰብ፤ የሀገሬን እግር ኳስ የት ነዉ ብሎ ?ለመመልከት ለሚገባ አዲስ ታዳሚ ኣላስፈላጊ ድርጊቶችን ቢመለከት ደስ የማይል ነገር ከስታድየም ይዞ ይወጣል። እናም የሁለቱ ቡድን ደጋፊዎች ያላቸዉን ተፆኖ ለመልካም ነገር ቢያዉሉት የተሻለ ነዉ እንላለን።

 

 

የተጫዎች ተፆኖ በተጫዎች በኩል ላለመሸነፍ በሚደረግ ጥረት ስሜታዊ ሊሆኑ ይችላሉ ።የነሱ በስሜት ሆኖ ኣላስፈላጊ ድርጊት ማድረግ በጨዋታዉ ድምቀት ላይ የራሱኑ ተፆኖ ይፈጥራል ።በዚህ ረገድ ተጫዎች በተቻላቸዉ መጠን ለነገሮች ትኩረት ቢሰጡ እንላለን። . . በመጨረሻም ሁሉም ከጨዋታዉ በፊት ያለዉን ነገር በተግባር የሚያሳይበት በጨዋተዉ ሂደት ብቻ ተነጋግሮ ከስታድየም የሚወጣበት የእግር ኳስ ጨዋታ እንዲሆን ተመኝሁ ። መልካም ጨዋታ ለሁለቱሙ ክለቦች ድል ለምትደግፋት ክለብ::

ምስል ክሬዲት-EBS

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.