ማርሽ ቀያሪው (ወዲ ይፍጠር)

0
1190
Yifter (#191), Nyambui (#649), and Maaninka (#208) at the 1980 Summer Olympics

በቀድሞ ጊዜ በቴሌቪዥን መስኮት በሚታይ የስፖርት ዝግጅት መግቢያ ላይ የሞስኮኑ ድል ሲያሸንፍ የሚያሳየሁን ምስል ሁሌም ከአእምሮ የማይጠፋዉ በተለይ የዚህ ሰዉ አራራጥ ካሸነፍ በኋላ እጅኑ ወደ ላይ የሚያረገዉ ድርጊት አይዘነጋኝም።ምሩፅ ይፍጠር በሙኒክ ኦሎምፒክ 10000ሜትር ሶስተኛ ሲወጣ በ5000 ሜትር ደግሞ ወደ ዉድድሮ ስፍራ ዘግይቶ በመድረሱ ሳይሳተፍ ቀርቷል። ሌላም ምክንያት ይሰጣል ያልተሳተፈበት ። ወደ ሀገር ቤት ሲመጣም እስር ነዉ የገጠመዉ። በመቀጠል ተሳትፉን ያረገዉ ኦሎምፒክ የድርብ ድል ባለቤት የሆነበት ዉድድር ሞስኮ ነዉ። በነገራችን ላይ ይህ ዉጤት ጀግናዉን አትሌት ሀይሌ ያነሳሳ ለዛሬ ስኬቱ መነሻ የሆነዉ የምሩፅ ዉጤት ነዉ ።ሀይሌ እንደተናገዉ” ሀገር ቤት ሳለሁ በሬዲዮ የምሩፅን ድል በምሰማበት ጊዜ እንደሱ ለመሆኑ ተነሳሁ” ይላል ።

 

ሌላዉ ከዚህ ጋር ሊነሳ የሚገባዉ ምሩፅና አብዮት አደባባይ ያለዉ የመሮጫ ቦታ።ይህ መሮጫ ቦታ ምሩፅ ሞስኮ ላይ በማሸነፍ መነሻ ስሜት በደርግ ጊዜ መሰራቱ ነዉ። .ሩጫ ካቆመ በኋላ በአሰልጣኙነት ቀጥሎ ነበር። ነገር ግን በወቅቱ በነበረ አንዳንድ ችግር ከሩጫ አሰልጣኙነት ወደ ቼዝ ፌዴሪሽን አዛወሮት በዚህ ተበሳጭቶ ሀገር ጥሎ ወደ ካናዳ ተሰደደ ። ብዙም ክብር ያልተሰጠዉ ይህ ሰዉ ህይወቱ አልጋ ባልጋ አልሆነለትም ፤ብዙ ችግሮችን አሳልፎ።  እነኛ በሞስኮ አደባባይ አለም ያስደመሙ እግሮቹ ላለፉት ወራት ላይ መንቀሳቀስ አቅጦቸዉ በዊልቸር ሲንቀሳቀሱ ነበር። ምሩፅም በህመሙ ወቅት ብዙ ማዉራት ባይችልም ነገር ግን የኢትዮጱያ ህዝብ ፀሎት እንዲያረግልኝ እፈልጋለሁ ሲል በሀዘኔታ አዉርቶ ነበር።  እናም ይህ ሰዉ የሀገር ባለ ዉለታ ኢትዮጱያን ብሎም አፋሪካን በትልቅ መድረክ ያስተዋወቀ ጀግናችን ነበር ማለት ልንጀምር ነዉ ከዛሬ በኋሏ ።  ዛሬ ረፋድ እንደተሰማዉ በሀገረ ካናደ በህክምና ላይ እያለ በ74 አመቱ ህይወቱ አልፋለች።በዚህ አጋጣሚ ድረገፃችን የተሰማዉን ሀዘን እየገለፀ ለመላዉ ህዝባችን መፃናናትን እንመኛለን። ክብር ለምሩፅ ይፍጠር!!!

በዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.