ከቀኃሦ እስከ አዲስ አበባ

0
1342

በዳግም ታምሩ
ሁሌም ስመለከተዉ ይገዝፍብኛል ፤ሁሌም ሳየዉ ትልቅነቱ ይታየኛል ።ለሀገሪቱ ለረጅም ጊዜ በብቸኝነት ሰርቷል ። በተለይ በቀደምት ሰዎች ዘንድ ትልቅ ትዝታ ያለዉ ስፋራ ነዉ።አይረሴ ጊዚያትም የነበረበት ቦታ።
.
.
√ በሴካፋዉም ጮቤ የተረገጠበት ” ከእንደተመኘሁት አገኙዋት እስከ ይትባረክ ዘላለም” ተብሎ የቴዘመበት ስፍራ ።

√ በብቸኝነት ሶስት አፍሪካ ዋንጫ ያስተናገደ ። መጀመሪያዉን ያስተናገደዉን የአፍሪካ ዉድድር ዋንጫዉ እዚሁ የቀረበት ስፍራ።
√ የወጣቶችንም የአፍሪካ ዋንጫም የተካሄደበት ።የቀድሞ የአሁኑም ክለቦች በእግር ኳስ ህዝቡን ያስደሰቱበት ።
.
√ ከይድነቃቸዉ ተሰማ እስከ ሳላዲን ሰኢድ የነገሱበት ቦታ ።
√ ተመልካቾችና ደጋፊዎች ረጅም ሰልፍና አድረዉ ጨዋታ የተመለከቱበት።
√ አትሌቶች በቅርቡ ተቃዉሞቾን ያስተጋቡበት ስፍራ።
√ ሀገሪቷን በተለያየ ጊዜ የመሩ ሰዎች ማለትም ከአፄ ሀይሌ ስላሴ እስከ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ድረስ የረገጡት ቦታ።
√ በታዋቂ ድምፂያኖችና በባንዶች ታላላቅ ኮንሰርቶች የተካሄደበት ፤ታማኝ በየነ ህዝብ ለህዝብ ላይ ፖለቲካዊ ይዘት ዘፈኖቹና ንግግሮችን ያረገበት።
√በኢህአፖ ዘመን ትልቅ መሸሸጊያና መገናኙ ስፋራ የነበረዉ እዚሁ ነዉ ።
√ በቅርብ አመታትም የ አህጉር አቀፍ አትሌቲክስ ዉድድሮች የተካሄደበት። ስለማን እያወራዉ መሆኑ አሁን የተረዳቹ ይመስለኛል ።
.
.
፠ በቀድሞ መጠሪያዉ ቀኃሥ ስታድየም በአሁኑ ስያሜዉ አአ ስታዲየም ነዉ።ስታድየሙ በሀገሪቷ የተካሄድ የተለያዩ ክንሆኖቹንማለትም ስፖርታዊ፣ፖለቲካዊ ማህበራዊ ፣ ሀይማኖታዊና መሰል ኩነቶችን እንዳስተናገደ ከላይ በተፃፈዉ ነገር መገንዘዘብ ይቻላል።
.
.
ይህ የ60 አመቱ አዛዉንቱ ስታዲየም የተለያዩ ታሪኮች ቢኖሩትም ለዛሬ ግን በስታድየም ዉስጥ ስለሚገኙ ስፋራዎች ስያሜ አወጣጥ ጥቂት እንበላቹ ።የመጠሪያዎቹ መነሻቸዉ አብዛኛዎቹ በድንገትና በነበረዉ አጋጣሚ የተሰጣቸዉ መሆኑ ነዉ ።በዚህ ስያሜ ዙሪያ ሌሎች ታሪኮችም ካሉ ለመቀበል ዝግጁ ነን ።
.
.
•ካታንጋ


ከኮንጎ ካታንጋ ከዘመቻ የተመለሱ አርበኞች ስፖርታዊ ዉድድሮች ለመመልከት ብዙ ጊዜ የሚመርጡት ቦታ የሜዳዉ አማካኙ ስፍራ ላይ ይቀመጡ ነበር ።እና ህዝቡ የት ነህ ሲባባሉ እዛ ከካታንጋ የመጡት ሰዎች የሚቀመጡበት ጋር በመባባል ነበር። አሁን ያለሁን ካታንጋ የሚለዉን ስያሜ የተገኙዉ ።
.
.
•ዳፍ (ፋሲካ በር)
ዳፍ የሚለዉ መነሻ አሁን በስታዲየሙ ዉስጥ በሚገኙ የስክሪኑ ቦታ ላይ የDAF አዉቶቢስ ማስታወቂ ለረጅም ጊዜ ተሰቅሎ የነበረ በመሆኑ ስያሜዉን አግኙቷል ።ሌላም ስም አለ ፋሲካ በር ።በቦታዉ ላይ ፋሲካ ዲባይ የሚባል ሰዉ በእግር ኳስ ያበደ ኳስ ሲመለከት ቁጭ ብሎ ማየት የማይችል ፤ከአንድ ጫፍ እስከ አንዱ ጫፍ በሮጫ የሚመለከት፤የተለያዩ ድርጊቶችን እያሳየ ህዝቡኑ የሚያዝናና፤ አንዳንዴም ጨዋታዉን እዛዉ ላሉት በድምፁ የሚያስተላልፍ አይረሴ ሰዉ ስለነበር ፋሲካ የሚለዉን መጠሪያ ያገኙዉ።
.
.
•ሚስማር ተራ
mismar-tera
የዚህ ስያሚ ቀደምት ደጋፊዎች እግር ኳስ ለማየት በሚፈልጉበት ጊዜ የተገኙ ነዉ።ለነገሩ በወቅቱ ህፃናት የነበሩት ሰዎች ሲናገሩ ስታዲየም መግባት ገንዘቡ በጣም ዉድ ስለ ነበር እና የራሳቸዉን ዘዴ ይጠቀሙ እንደነበር ይናገራሉ።ይህም በጊዜዉ የካምቦሎጆ ዙሪያው ምንም አይነት ሱቆች አልነበረም እና ልጆቹ የስታድየሙን ግንቡን በሚስማርና በሌሎች ነገሮች እየበሱ ይመለከቱ ነበር። ( ቀዳዳዉን በትንሽ ፍራንክ እያከራዩ የሚያሳዩ ግለሰቦች ነበሩ)አብዛኛዉ ሰዉ ደግሞ በዚህ ብልሀት ስፖርቱኑ ይመለከት የነበረበትን ስፍራ ሚስማር ተራ አሉት ።
.
.
•አበበ ቢቂላ በር
ይህ ስያሜ የተገኙዉ የመግቢያዉን በር መነሻዉ ያደረገ ነዉ 11 ቁጥር ፤ቁጥሩ አቤ የመጀመሪያዉን የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያ ለኢትዮጱያም ብሎም ለአፍሪካ በሮም አደባባይ ሲያገኙ የለበሰዉ የማልያ የመሮጫ ቁጥር ነዉ።
.
.
•ከማን አንሼ
kemananishe
የዚህ መነሻ ደግሞ አጠገቡ የሚገኙት የስታድየም ቦታ ማለትም ከሌሎቹ ቦታ የተሻለ ነገር ያለበት (ፀሀይ በሚሆንበት ጊዜ ከጥላ ፎቅ ጋር ስለሚጋራ )በመሆኑ ህዝቡ ከማንስ አንሼ ነዉ በሚል ስሜት ስለሚገቡ የተሰጠ ስያሜ ነዉ።
.
.
ጥላ ፎቅና ክብር ትሪቩን ደግሞ ስያሚያቸዉ ግልፁ መሰለኝ ካላቸዉ አገልግሉትና ከሚሰጡት ነገር የወጣ የስታድየም ክፍል ናቸዉ።

በዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.