ይርጋለም ላይ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ተቃዉማቸዉን አሰሙ፤ አአ ላይ የስታድየም ፓዉዛ ጠፋ ጎንደር ላይ ለበጎ አላማ የስታድየም ገቢ ተደረገ

0
1210
አንጋፋዉ የአአ ስታድየም ፓዉዛዎች በመጥፋት ጨዋታን ለተወሰነ ደቂቃ አቋርጣል ።ጎንደር ላይ ፋሲለደስ ስታድየም አሁንም ለበጎ ፋቃድ አገልግሎት የስታድየሙን ገቢ አድሩጓል ። በ6 ተኛዉ ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች ሶስት ክለቦች በደረጃ ሰንጠረዥ አናት ላይ በእኩል ነጥብ ተቀምተዉ በግብ ክፋያ ተለያይተዋል ።
 የዚህ ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች የተደረጉት ሁሉም በእለተ እሁድ ሲሆን አአ ላይ ሁለት ጨዋታዎች የተካሄዱ ሲሆን ዘጠኝ ሰአት ላይ ደደቢት ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ያስተናገደዉ ጨዋታ በደደቢት 2 ለ0 የበላይነት ተጠናቋል ።በጨዋታዉ በደደቢት በኩል አይናለም ሀይሉ በቀጥታ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወቷል።ሌላዉ ደደቢት በሊጉ ካገባቸዉ 7 ጎሎች 6 ያገባዉ ጌታነህ ከበደ ነዉ ። . በሜዳዉ ወልዲያን ያስተናገደዉ አዳማ ከነማ ድል በማድረግ ወደ ሊጉ ተፎካካሪነት ያለዉን ጉዞ በቅርብ ርቀት አስቀጥሏል 1 ለ0 በማሸነፍ ነዉ። አርባምንጭ የተጓዘዉ የአአ ከነማ 3 ለ1 በሆነ ዉጤት ተሸንፉል ።
በሳምንቱ በሊጉ ከተካሄድ ጨዋታዎች ሰፊ ግብ የተቆጠረበት ጨዋታ ነዉ።በፋሲለደስ ስታድየም ሀዋሳን ያስተናገደዉ ፋሲል ከነማ በአቻ ዉጤት ጨዋታቸዉን ፈፃመዋል።ከጨዋታ ጎን ለጎን የስታድየሙን ገቢ ለበጎ ነገር የተደረገበት ጨዋታ ነበር ።የቀድሞ የፋሲል ከነማ የተስፋ ቡድኑ ና በአሁኑ ሰአት የዩኒቨርስቲ ተማሪ ለሆነዉ ሁለት ኩላሊቶቹ ስራ መስራት ላቆሙበት ወጣት ጥበበ ለህክምና ወጪ እንዲሁል የተደረገበት ጨዋታ ነዉ ። በሳምንቱ ሲጠበቅ ከነበሩ ጨዋታዎች ግንባር ቀደም ቦታ የነበረዉ ይርጋለም ላይ ሲዳማ ቡናከ ቅ ጊዮርጊስ ነበር ።በዉጤቱም 0 ለ0 በሆነ አቻ ነበር የተለያዩት። በጨዋታዉ መጠናቀቂያ ከአአ የተጓዝ የጊዮርጊስ ደጋፊዎች በተጫዎቾቹ ና በአሰልጣኙ ላይ ተቃዉማቸዉን አሰምተዋል።በቡድኑ ደስተኛ አለመሆናቸዉ ደጋፊዎች ይናገራሉ።
ምስል ከፈረሰኞቹ ገፁ የተወሰደ
ምስል ከፈረሰኞቹ ገፁ የተወሰደ
 ወደ ወላይታ ሶዶ ያቀናዉ የኢትዮጱያ ቡና ነጥብ ተጋርቶ መቷል። ድሬዳዋ ያቀናዉ ኢትዮጱያ ንግድ ባንክ በሊጉ ሁለተኛዉን ድል አስመዝግባል። ከወራጅ ቀጠናም ራሱንጰ ከፍ ማድረግ ችሏል።በሳምንቱ ከሜዳ ዉጪ ያሸነፈ ብቸኛዉ ቡድን ያድርገዋል ንግድ ባንክን።የ6 ተኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ የነበረዉ አአ ላይ 11:30 የተደረገዉ የመከላከያና ጅማ አባቡና ጨዋታ ነዉ ።ጨዋታዉ በሁለቱ ክለቦች ማራኪ እንቅስቃሴ የታየበት ቢሆን የማታ ማታ ድል ለባለ ሜዳዉ መከላከያ ሆኖል።1 ለ0 በሆነ ዉጤት ።በጨዋታዉ 70 ደቂቃ ላይ በስታድየሙ የሚበሩት ፓዉዛ አብዛኛዉ ሀይል መስጠጣቸዉና አቁመዉ የነበሩ በመሆኑ ጨዋታዉ ለተወሰነ ደቂቃ ተቆርጦ ነበር ።
በዚኛዉ ሳምንት የሊግ ጨዋታ ክለቦች የተቀራረበ ነጥብ ላይ እንዲገመጡ ያረገ ዉጤት የተስተናገደበት ነዉ።ጊዮርጊስ ፣ደደቢትና ኣዳማ በኩል አስራአንድ ነጥብ የሊጉ አናት ላይ በተርታ የተቀመጡ ሲሆን በግብ ክፍያ ተለያይተዋል።ግርጌ ላይ ሀዋሳ ከነማ እና አአ ከነማ በኩል አምስት ነጥብ 14 ተኛ እና 15 ተኛ ሲቀመጡ ኤሌክትሪክ በ አራትነጥብ 16 ተኛ ይገኛል። ጌታነህ ከበደ ለብቻዉ የኮከብ ግብ አግቢነቱን በስድስት ግብ እየመራ ይገኛል።
በዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.