ለኢትዮጱያ እግር ኳስ ለአበረከተው አስተዋፅኦ የኳስ ዶክተሩ መንግስቱ ወርቁ አሁንም ክብር ይገባዋል በማለት ዛሬ አስታዉሰነዋል።

0
1265

ትዉስታ ኢንስትራክተር መንግስቱ ወርቁን፡፡ በኢትዮጱያ እግር ኳስ በተጫዎችነት በአሰልጣኝነት እንዲሁም የመጀመሪያዉ ኢንስትራክተር በመሆን ለረጅም አመት ያሳለፈዉ የኳስ ዶክተሩ መንግስቱ ወርቁ እነሆ ዛሬ ታህሳስ 8 በህይወት ካጣናቸዉ ስድስት አመታቸዉ ተቆጠረ ። መንግስቱ ብዙ ተቀፅላ ስሞች የነበሩት ነበር ለመጥቀስ ያክል ጎንደሬዉ፣ፊት አዉራሪና የኳስ ዶክተሩ የሚጠቀስ ናቸዉ ። ሌላዉ መንግስቱ ሲነሳ የማይረዘነጋዉ ነገር እሱና 8 ቁጥር አይረሴ ናቸዉ።  የመኪናዉ ታርጋ የመጨረሻዉ ቁጥር 8 ነዉ ።

ሎተሪ ሲቆርጥ የመጨረሻዉ ቁጥር 8 ነዉ። የሚለብሰዉ ማልያ ቁጥር 8 ነዉ። ህይወቱ ያለፈዉ ታህሳስ 8 ነዉ።  የተጫወተበት ክለብ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሚለዉ ፊደል ሲቆጠር 8 ነዉ። እና ለኢትዮጱያ እግር ኳስ ለአበረከቱት አስተዋፅኦ መንግስቱ አሁንም ክብር ይገባዋል በማለት ዛሬ አስታዉሰነዋል።

በዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.