እኛ የዛኔዋቹ‘ና ናፍቆት!

0
985

እኛ የዛኔዋቹ‘ና ናፍቆት! ባልጠፋ ነገር ድሮ ይናፍቀኛል! የፊቱ ደሞ ገና ሳስበው ግሽግሽ ያደርገኛል! ሎሚ ይዤ ነው ስለ ፊቱ የማሰላስለው ተስፋ መቁረጥ ምልክቱ እንግዴ ይሄ ይመስለኛል! ። ላይብረሪ በሌለበት ጎግል እና ኢንሳይክሎፒድያ፣ ዊክፒድያ በማይታሰቡበት ዘመን መማሬን ዞር ብዬ ሳስብ ናፍቆቱ ውስድ ያደርገኛል ! ።

እኛ የዛኔዋቹ ካሁኖቹ በንቃት ከፍ እንደምንል የማውቀው የኛ ጊዜ ተማሪ 12 × 12 ስንት እንደሆነ ከመቅስፈት ያለ ሳይንቲፊክ ካልኩሌተር የሚመልሰው አመት ሙሉ ከሚማርበት ደብተር ጀርባ ያሉትን ጊዜ ቤቶች ሂሳብ እንደ ታሪክ የመሸምደድ ችሎታው ድንቅ ስለነበር ነው። ። በፊት መስከረም ሲመጣ ወደ ተማሪ ቤት መሄድ ያምረኝ እንደነበረው ላንጉረር በላንጉረር ለብሼ ያልተፃፈባቸው አምስት 16 ሉክ ደብተሮች እንደያዙ ተማሪ ላይ መሸለል ያምረኛል የዛራና ቻንድራ ግራፊክስ ያለበት ደብተር ሳይ አስራ ስድት ሉክዋ ላይ ያለችው እርግብ‘ና ብእር ትዝ ብለውኝ እነሱን እናፍቃለሁ ……እርግብዋን እያየን ተምረን ለምን የሰላም አምባሳደር መሆን አቃተን ብዬ ስጠይቅ ከርማለሁ! ። መስቀል ሲቀርብ ለዳመራ ፎርስት መግባቱ ሁላ በ አይኔ ውልብ ይላል ………ያኔ አድቬንቸራችን ነበራ ለኛ…… አሁን ጎጂ ባህል ሆንዋል አሉ! ………አዋ ግን ጎጂነቱ ዛፍ ቆርጦ ወረቀት ካደረጉ ቡሀላ ወረቀቱ ላይ ዛፍ መቁረጥ ነፍስ ማጥፋት ነው ብሎ መፃፉስ ጎጂ ልማድ አለመሆኑ እስካሁን ያጠያይቀኛል!? ።

እኛ የዛኔዋቹ አንድ መፅሀፍ ለአምስት ለአምስት ቤተሰብ ተያዥ አሲዘን የወሰድን ከመፅሀፍ ላይ በጋዝ ስእል የቀዳን!…… ቁጥር እንኮ ከ አንድ ነው የሚጀምረው ለምን 0 ክላስ ተብለን ተማርን ብለን ያልጠየቅን ………ለምን ግን ከባዶ ክፍል አስጀመሩን?…… ። እኛ የዛኔዋቹ በዴይ ያላበድን crazy day ፣ water day ፣ oldies day እያልን ብላክ መንዴይ ካልተከበረ ብለን ግብ ግብ ያልያዝን ቀጥ ለጥ ብለን ያርበኞች ቀን ፣ የላብ አደሮችን ቀን ፣ የድል አድራጊዋች እና የበጎ አድራጊዋችን ቀን እየጠበቅን ሞቅ አድርገን ያከበርን! ። እኛ የዛኔዋቹ በግማሽ ቀን ግማሽ ደርዘን የትምህርት አይነት ተምረን እዚ የደረስን እኛ የዛኔዋቹ የደብዳቤ ዘመን ፍቅረኛሞች የቴፕ ካሴት አድናቂዋች ………ዳውንሎድ ማድረገን አንዱን ካሴት በአንዱ በመደምሰስ ከሬድዬ በመቅዳት ልምድ የቀሰምን! ።

ምን እኝህ ብቻ ይገርማቹሀል ጭራሽ የድሮዋ ኢትዬጵያም ትናፍቀኛለች! የድሮ ስርአት ናፋቂ በሉኝ ደሞ! ብቻ ከወደፊት ይልቅ ወደ ድሮ እንድሰደድ ያስገድዱኛል ………አይ እኛ የዛኔዋቹ! ።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ፀሀፊ: #ይሄ_መሳይ_እስከዳር_አበራ @[100012704267399:0]

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.