አስረጂኛ?

0
970

ዩኒቨርስቲ መግባት ለኔ ዩኒቨርስን ለይቶ የማወቅ ያህል ከባድ ነበር! ። አራት ነጥብ ያለው ነው የሚገባው ሲባል ሰምቼ በክላሰር ትልልቅ አራት ነጥቦችን በፓርከር አድምቄ ይዤ ሄጄ ዳሬክተሩን እስከማናገር ደርሼ ነበር……… ለካ በፈተና ተሰልቶ የሚሰጥ ውጤት እንደሆነ ያወኩት ዘግይቼ ነው! ። ከምማራቸው ትምህርቶች ሁሉ ሂሳብ ለኔ እጅግ ቀላሉ ትምህርት ነበር…… ለምን ብትሉኝ ሃሳብ በጣም አበዛ ነበር የማልደምረው የማልቀንሰው ጉዳይ የለም! አሁን የኢትዬጰያ ህዝብ ቁጥር መቶ ሚልየን ከደረሰ ሀገራችን እምዬ ኢትዬጵያን በሊዝ ብንሸጣት ስንት ስንት እንደሚደርሰን ታውቃላቹ……? እሱን ሁላ አስልቼ ደርሼበታለሁ… …ግን ይሄን ስሌት በጉጉት የሚጠብቅ ካለ ባንዳ መሆን አለበት እንዴት ሀገር ይሸጣል ነገሩን ነው እንጂ ሆ!? ። መቼ ለት ሂሳብ ታስተምረኝ የነበረች መምህሬ ፀበል ፃድቅ ተጠርታ ሰፈር እንደኔ ከደረሱ ጎደኞቼ ጋር በተቀመጥቁበት ጠርታ የጋሽ አካሉ ቤት በየቱ ጋር ነው አለችኝ አካሉ አካሉ ያ ሸፋፋው ሰውዬ? ……አዋ እሱ!…… ይገርማቹሀል እሱ ሲያልፍ ውሀ እንደ ቋጠረ አስፈልት ዳር እንዳለ ኩሬ መኪና ረግጦት ውሀ እንደሚረጭ ጮሮቃ በፍጥነት ካለሸሸነው የእግሩ ሽፈት በቆምንበት በጠረባ ይጥለናል ግን እኮ በጀቱ የሌለ ነው እሱ ሰውዬ…… በየ ወሩ እሱ ቤት ፀበል ፃድቅ አይጠፋም ግን አውቆ ማኖ ሲያስነካ ነው ይሉታል ………የሰፈሩ ሰው ግብር ነው ፃድቅ አደለም ይላል ………እንዲ የሚሉት እሱ ሲደግስ የማይጠራቸው እትዬ አረገዱ ናቸው። ።

እረ ንገረኝ ስለምን እያሰብክ ነው ጭልጥ ብለህ የሄድከው የአካሉን ቤት ጠቁመኝ እንጂ አለችኝ?……… ውይ በሃሳብ ሰጥሜ እኮ ነው እየውልሽ በዛ በኩል እንደታጠፍሽ ተዘቅዘቂ አልኮት……… ምን ብላ ጮህችብኝ ! …………ተዘቅዘቂ ታገኝዋለሽ አልኮት እረ በሚገባኝ ቋንቋ ንገረኝ አለችኝ ………ለካ ሂሳብ አስተማሪ ነች በሂሳብ ቋንቋ እንዲ ብዬ ነገርኩዋት እየውልሽ ይሄን መንገድ ይዘሽ ትሄጂና አደበባዬን በመቶ ሰማንያ ዲግሪ ዞረሽ የመንገዱ ጠርዝ ላይ የኤክስና ዋይ ኮርድኔት ጋር ስትደርሺ ኤክስን በግማሽ አባዝተሽ ከታጠፍሽ ቡሀላ አስር ማይል እንደሄድሽ ትቆሚና ከፊት የሚታየውን ቆሞ የቀረ ያረጀ መኪና እርቀቱን በእግርሽ 3/4 ኛ አካፍለሽ ሪዛልቱን ማለትም ቤቱን ታገኛለሽ አልኩዋት! ምን አለችኝ? ያው እንዳልኩሽ ነው አልኩዋት? አልገባኝም በግልፅ ልታስረዳኝ ትችላለህ አለችኝ! ሂሳብ አስተማሪ አደለሽ? እና ብሆን ይሄን እንዴት በቶሎ ልረዳ እችላለሁ? ታድያ ዘጠና የሂሳብ ደረቅ ጥያቄ በስልሳ ደቂቃ ሰርታቹ ካላመጣቹ ምትይን በግልፅ ልታድረጂኝ ትቺያለሽ አልኳት? ! እኛም እኮ ይሄን በቶሎ መረዳት ይከብዳል አይከብድም እ? ።።።።።።።።።።።።።።።

#ይሄ_መሳይ_እስከዳር_አበራ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.