በአቻ ዉጤትና ና በቀይ ካርድ ብዛት የታጀበ ሳምንት!

0
844

በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት አአና ክልል ላይ በተካሄድ የ5 ተኛ ሳምንት የሀገሪቶ ትልቁ ሊግ ጨዋታዎች ቀጥለዉ ዉሏል ። የሳምንቱ መክፈቻ ጨዋታ ያደረጉት አአ ላይ በእለተ ቅዳሜ ዘጠኝ ሰአት ሲል በሜዳዉ ኤሌክትሪክ አርባምንጭ ከነማን አስተናግዶ በጎል አቻ በመለያየት በተከታታይ የአቻ መዉጣት ዉጤቱኑ አስቀጥሏል ።በጨዋታዉም በሁለት ቢጫ የመሀል አማካኙ ዳዊት እስቲጢፋኖስን በሁለተኛዉ አጋማሽ አጥቷል።የዚህን ጨዋታ ተከትሎ ሁለቱ በሊጉ በቡና ሴክተሩ ድጋፍ የሚደረግላችዉን ክለብ 11:30 ላይ በማገናኝት ነበር ።ኢትዮጱያ ቡና ከሲዳማ ቡና ጨዋታዉም ኢትዮጱያ ቡና በዘንድሮ ሊግ ያሸነፈበትን የመጀመሪያሶስት ነጥብ 2 ለ1 በሆነ ዉጤት ኣሳክቷል ።

በእለተ እሁድ ደግሞ በሊጉ ከተካሄድ ጨዋታዎች ስድስት ጨዋታዎች አራቱ ያለግብ 0 ለ0 ያለቁ ጨዋታዎች ነበሩ ። ጅማ አባቡና ከደደቢት ወልዲያከ ከፋሲል ከነማ ወላይታዲቻከ ድሬዳዋ ከነማ ቅ/ጊዮርጊስ ከኣዳማ ከነማ ከላይ የተካሄድ ጨዋታዎች ያለግብ የተለያዩ ክለቦች ናቸዉ።

ሌላዉ ሀዋሳ ላይ በዉዝግብ፣በቀይ ካርድና በቢጫ ካርድ የታጀበዉ ጨዋታ በሳምንቱ በከፍተኛ ግብ አቻ በመዉጣት 2 ለ2 ተጠናቆል ።ሀዋሳ ከነማ ከመከላከያ በጨዋታዉ አራት ቀይ የታየ ሲሆን ከሀዋሳ በኩል ሁለት ተጫዋቹች ከሜዳ ቀይ ካርድ ያገኙ ሲሆን ሌሎቹ ሁለት ተጫዎች ደግሞ ከመጠባበቂያ ወንበር ላይ ያገኙ ናቸዉ ከሀዋሳ አዲስ አለም ተስፋዩ ከመከላከያ ታፈሰ ሰርካ መሆናቸዉ ነዉ። አ/አ ላይ እንደ ኢትዮጱያ ቡና ሁሉ የመጀመሪያዉን ነጥብ ያገኙዉ ኢትዮጱያ ንግድ ባንክ በመጨረሻ ደቂቃዎች ባገባቸዉ ሁለት ግቦች ከኋላ ተነስቶ 2 ለ1 ማሸነፍ ችሏል ።

በመጨረሻም ይሄን ማለት ወደድን በኢትዮጱያ እግር ኳስ ላይ ከግዜ ወደግዜ ባህሪያት ያልሆኑ በግድ በየሳምንቱ ባህሪያችን እየሆነ እየመጣ መሰለኝ ፤በተጫዎችበኩል የዳኛን ዉሳኔ በአግባቡ አለመቀበል ።ደጋፊ ስፖርታዊ ጨዋነትን በሚገባ እያመነ ባለበት በዚህ ሰአት ላይ ።በአብዛኛዉ ክለቦች ላይ የሚገኝ ተጫዎች አላስፈላጊ ድርጊትን እያከናወኑ ይገኛል ። እነዚህ በተጫዎች ላይ የምንመለከታቸዉ አላስፈላጊ ነገር ብዙ ቁጥር ደጋፊ ያላቸዉ ክለቦች ላይ በደጋፊ ላይ የሚፈጥሩዉ ነገር ጥሩ ስላልሆነ ተጫዎች ሚዲያ ላይ ብቻ ሲመጡ አይደለም ስለ ስነምግባርና ስለ ስፖርታዊ ጨዋነት መናገር ያለባቸዉ በተግባር ሊያሳኙን እና ብሎም ለደጋፊዎቹ ትምህርት ሊሰጡ ይገባል ባይ ነን ።እዚጋ የዳኛዉ ዉሳኔ ሁሉ ልክ ነዉ እያልኩ እንዳልሆነ ልትረዱልኝ ይገባል ።በዚህ አጋጣሚ ዳኞችም ያለባቸዉን ክፍተት በሚገባ ተረድተዉ የተሻለ ነገር እንዲያሳዩን እንጠይቃል ።በሊጉ የሚዳኙት ዳኞች ከሁሉ ነገር ነፃ ሆነዉ የሚዳኙበት ነገር መፍጠርም ተገቢ መስሎ ይታየናል ። እናም የስፖርት ሜዳዎችን የመዝናኛ ቦታዎች እናርጋቸዉ የግጭትና የጥላቻ ቦታ ባናረገቻዉ ለስፖርቱ እድገት የተሻለ ነዉ እንላለን።

በዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.