የቀድሞ የኢትዮጱያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳት በሌላ የስፖርት ፌዴሬሽን ወደ ስፖርቱ በፕሬዝዳንትነት መተዋልና ሌሎች የሀገር ዉስጥ ዜናዎችና የሊጉ ጥቆማዎች

0
1349

የቀድሞ የኢትዮጱያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳት በሌላ የስፖርት ፌዴሬሽን ወደ ስፖርቱ በፕሬዝዳንትነት መተዋል።

የ2009 የኢትዮጱያ ፕሪሚየም ሊግ የ5 ተኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ቅዳሜና እሁድ በክልሎችና በዋናዉ ከተማዉ ቀጥለዉ ይዉላሉ ።

የዚህ ሳምንት የሊጉ መክፈቻ ጨዋታ በነገዉ እለት በሚደረግ የ9 ሰአት ጨዋታ ሊጉ ጅማሬዉን ያደርግል ።የጨዋታዉ ቦታ አአ ስታድየም ተጋጣሚዎቹ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከአርባምንጭ ከነማ ። አርባምንጭ ባለፈዉ ሳምንት በሊጉ ከፍተኛ ጎል አስቆጥሩ ያሸነፈ ብቸኛዉ ክለብ ሲሆን ኤሌክትሪክ በአንፃሩ አቻ የወጣበት ሳምንት ነበር ።ይሄ ጨዋታ እንዳለቀ 11:30 ላይ ስያሚያቸዉ ላይ ቡና የሚል መጠሪያ ያላቸዉ ክለቦች የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል ።ኢትዮጱያ ቡና ከሲዳማ ቡና ።በአራተኛዉ ሳምንት ዉጤት ወደ ኣዳማ ያቀናዉ ቡና ዉጤት ተጋርቶ መምጣቱ የሚታወስ ሲሆን በሲዳማ በኩል ሌላኛዉን የክልሉን ክለብ ወላይታ ዲቻን አሸንፎ በመምጣት በሊጉ ሰንጠረዥ ከጊዮርጊስ ጋር በእኩል ነጥብ ላይ ተቀምጦ በግብ ከፍያ ሁለተኛ ላይ ተቀምጦ ነዉ አምስተኛ ሳምንት ላይ በቡና ደርቢ የተገናኙት ። ቀሪዎቹ ሰባት ጨዋታዎች እሁድ ለት የሚከናወኑ ሲሆን ሁለቱ አዲስ አበባ ላይ ሲካሄድ ሌሎቹ በክልል የሚካሄድ ናቸዉ።

መልከ ቆሌ ላይ ሁለቱ ዘንድሮ ወደ ሊጉ የተቀላቀሉ የአማራ ክልል ክለቦችን ያገናኛል ወልዲያ ከነማ ከፋሲል ከነማ ።በፋሲል በኩል በሊጉ እስከ ሶስተኛዉ ሳምንት ድረስ ያልተሸነፈዉን ቅዱስ ጊዮርጊስ በአራተኛዉ ሳምንት አሸንፎ ነዉ ለጨዋታ የደረሰዉ ።በወልዲያዎቹ በኩል ደግሞ አአ ላይ ያደረጉት የመጀመሪያ ጨዋታ በመከላከያ ሽንፈት አስተናግደዉ ነዉ ለደርቢዉ ፍልሚያ የሚገናኙት። ጅማ ላይ በቴክኒክ ዳሬክተሩ የሚመራዉ ደደቢት ከጅማ አባቡና ይጫወታል ። ሶዶ ላይ ወላይታ ዲቻ ከ ድሬዳዋ ከነማ የሚያደርጉት ጨዋታ ሲጠበቅ ።

በአራተኛ ሳምንት ጨዋታቸዉ አንደኛዉ አሸንፎ ሌላኛዉ ተሸንፎ የሚገናኙ ናቸዉ በተመሳሳይ ዉጤት 1 ለ 0 ሲሆን ድሬዳዋከነማ አዲስ አበባ ከነማን በማሸነፍ ነበር በወላይታ በኩል በሲዳማ የተሸነፈበት ዉጤት ነዉ።ከላይ እንዳለሁ በተመሳሳይ ዉጤት አሸንፈዉና ተሸንፈዉ የሚገናኙ ክለቦች ሀዋሳ ላይ ቀጠሮ ይዘዋል ።ሀዋሳ ከነማ ከመከላከያ ።ሀዋሳ በደደቢት 2 ለ0 ተሸንፎ ሲመጣ መከላከያ በበኩሉ ወልዲያን 2 ለ 0 ያሸነፈበት ዉጤት ይጠቀሳል ። ሁለቱ የአአ ስታድየም የእሁድ ጨዋታዎች በ9 ሰአት የከተማዉ መስተዳድር ክለብ አዲስአበበ ከተማ ከ ኢትዮጱያ ንግድ ባንክ እና 11:30 ሲል የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኣዳማ ከነማ የሚጫወቱትም ጨዋታ ሌላዉ በሳምንቱ ከሚጠበቁና በሰንጠረዥ ላይ ለዉጥ ያመጣል ተብሎ የሚጠበቅ የሳምንቱ ትልቁ ጨዋታ ነዉ ።ኣዳማ ሰባት ነጥብ ላይ ተቀምጦ ሲጫወት ጊዮርጊስ በበኩሉ በዘጠኝ ነጥብ ላይ ሆነዉ ነዉ የሳምንቱን የመጨረሻ ጨዋታ የሚያደርጉት ።

በሳምንቱ መጨረሸ የቀድሞ የኢትዮጱያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳት ዶ/ር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ ወደ ስፖርት ፌዴሬሽን ፕሬዝዳትነት ከአመታት በኋላ መመለሳቸዉ በስፖርቱ ተከታታይ ዘንድ አግራሞት ጭራል ።በአዲሱ የፕሬዝዳትነት ሹመትም የቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን በመሆን መሾማቸዉን ሰምተናል ።በእሳቸዉ የእግር ኳስ የፕሬዝዳትነት ዘመን ሀገሪቷ በእግር ኳስ ታግዳ እንደነበር የሚታወስ ነዉ።

 

ሴቶች እግር ኳስ  በዘንድሮ የሴቶች ሊግ በመጀመሪያዉ ምድብ የሚገኝዉ ደደቢት የተጫወታቸዉን ሁለት ጨዋታዎች በማሸነፍ በ 6 ነጥብ ይገኛል።ይሄም ሆኖ ሳለ ክለቡ አከባቢ ባገኝነዉ መረጃ መሰረት ለተጫዎቹ በዘንድሮ አመት ምንም አይነት ክፋያ እና የፊርማ ገንዘብ አለመስጠቱ አረጋግጠናል።

15416146_1261356630602428_922720764_n

በተጫዎቹም በኩል ደሞዛቸዉ ባለመከፈላቸዉ ደስተኛ እንዳልሆኑ ከአገኝነዉ መረጃ ደርሰንበታል ።ተጫዎቹ በተደጋጋሚ ገንዘባቸዉን የጠየቁ ሲሆን በክለቡ በኩል ግን ቆይ ጠብቁ የሚል ምላሽ ብቻ መኖሩን ተገንዝበናል።

በዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.