ስርአት አልበኝነት በኢትዮጱያ እግር ኳስ አሁንም እየቀጠለ ነዉ

0
1395

በዳግም ታምሩ

በዘንድሮ የኢትዮጱያ ፕሪምየም ሊግ አራተኛ ሳምንት ጨዋታ ኣዳማ ላይ ኣዳማ ከነማ ከኢትዮጱያ ቡና በነበራቸዉ ጨዋታላይ ጨዋታዉ ሊጠናቀቅ 5 ደቂቃ ሲቀረዉ በተለምዶ ካታንጋ በሚባለዉ በኩል ስታድየም ዉስጥ ባልገቡ ከዉጪ በተወረወረ ድንጋይ በደጋፊዎች ላይ በመገፋፋትና በመወዳደቅ ጉዳት ደርሳል ፤በሁለቱሙ ደጋፊዎች ዘንድ ።ለዚህ ክስተት መነሻ ናቸዉ ብዬ ያሰብኳቸዉ ችግሮች መነሻቸዉ ከታች እንደሚመለከተዉ ታዝቤለዉ ከጨዋታዉ በፊት የነበሩ እና የታዘብኳቸዉ ነገሮች . .

  • ቸልተኝነትና እንዝላልነት የነበረ የጥበቃ አግልግሎት ።

ለዚህ እንዝላልት ምሳሌ የሚሆነዉ ደጋፊዉ ወደ ስታድየም ሲገባ የሚገዛዉ ትኬት ሳይቀደድ በድጋሚ በህገወጥ መንገድ ተሰብስቦ በድጋሚ ሽያጭ ላይ ሲዉል አስተዉለናል ።የሚያስገርመዉ ደግሞ ባጅ አርገዉ ክለቡ የወከላቸዉ ሰዎች መሆኑ ይበልጥ ያሳፍራል ። .

  • ሌላዉ በኣዳማ አበበ ቢቂላ ስታድየም በካታንጋዉ በኩል የተሰራዉ “መቀመጫ “።

ለመቀመጫነት የተባለዉ የተሰራዉ ሙሉ ለሙሉ በእንጨት ርብራብ ተደርጎ ለእግር ኳስ ደጋፊዉ ምቹ ያልሆነ መሆኑ መገንዘብ በጣም ቀላል ነገር ነዉ።በተለይ የእግር ኳስን ባህሪ ለሚረዳ ማንኛዉም ሰዉ።በነበረዉ መገፋፋትም የእንጨት ርብራብ በመሆኑ የደረሰም ጎዳት መኖሩን ባየን ጊዜም መደረጉ ስህተት ነዉ። ነገርየዉ ለሌላ ነገርም ተሰርቶ ከሆነም ሰዉ እንዲቀመጥበት መፍቀድ ተገቢ አልነበረም። .

አሁንም ቢሆን እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ በስፖርታዊ ጨዋነት ዙሪያ የጀመረዉ ነገር ጥሩ ሆኖ ሳለ ነገር እየሰጣቸዉ ያሉት መፍትሄ የት ድረስ ያደርሰኛል የሚለዉን ትኩረት ማድረግ እንዳለበት ሊረዳ ይገባዋል ።ነገሮችን ወደ እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ብቻ እየጠኮምኩ ብቻ እንዳልሆነ ልብ ልትሉልኝ ይገባል ።ስፖርታዊ ጨዋነት ስፖርቱን የሚከታተል የማይከታተል የማንኛዉም ህዝብ ሀላፊነት ጭምር እንደሆነ የምንረዳ ይመስለኛል። እናም በዛሬ ኣዳማዉ ጨዋታ ላይ የተከሰተዉ መነሻ ከላይ የጠቀስኳቸዉ ችግሮች ማለትም በደፈናዉ የጥበቃ አገልግሎቱ የላላና ስርአት የሌዉ በመሆኑ የተፈጠረ ችግር ነዉ።

በመጨረሻም የዛሬ ኮሚሽነር የነበረዉን ነገር በሚገባህ ተረድተዉ ያለዉን ሁኔታ ለእግርኳስ ፌዴሬሽኑ ይገልፃሉ ብዬ እጠብቃለሁ ።ከባለፈዉ አመቱ ስህተቱ ተምሮ ፌዴሬሽኑ በቸልተኝነት ነገሮን ማየት እንደሌለበት በዚህ አጋጣሚ ኣፅኖት ሰጥቼ እገልፃለዉ።የጨዋታዉ ዉጤትም 1 ለ1 በሆነ ሁኔታ የተጠናቀቀ ነዉ።በቀዳሚነት ጎል ያገባዉ ኢትዮጱያ ቡና ተቀይሮ በገባዉ ዊልያም ሲሆን ግጭቱ በተፈጠረበት ጊዜ ደግሞ አዳማ ከነማ በሙጂብ ካሲም አቻ አድርጓል።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.