የ2009 የኢትዮጱያ ፕሪሚየም ሊግ የአራተኛዉ ሳምንት ጨዎታዎች::

0
856

የዚህ ሳምንት ጨዎታ መክፈቻ የሚሆነዉ ጨዎታ አአ ላይ በሚካሄድ አንድ ጨዎታ ጅማሮን ያደርጋል ። በ11:30 ደደቢት ከሀዋሳ ከነማ ።ደደቢት ዋና አሰልጣኙን ዮሀንስ ሳህሌ ከአባረር በኋላ በቴክኒክ ዳሬክተሩ አስራት ሀይሌ እየተመራ የሚደርገዉ ጨዋታ ነዉ ።ሀዋሳ በሊጉ የመጀመሪያ ማሸነፍ ካገኙ በኋላ የሚደርገዉ ግጥሚያ ሲሆን ደደቢት ደግሞ ወደ ማሸነፍ መንፈስ ይመጣል ተብሎ የሚጠበቅ የቅዳሜ ጨዋታ ነዉ ።

እንደባለፈዉ ሳምንት በዚህኛዉም ሳምንት ቀሪ ሰባት ጨዋታዎች የሚካሄድት በእለተ እሁድ ሲሆን፤ ሁለቱ በዋና ከተማዉ አአ ላይ ሲሆን አምስት ጨዎታዎች ደግሞ በክልል ከተሞች የሚደረጉ ይሆናል ። አርባምንጭ ላይ በሊጉ ታሪክ ንግድ ባንክ ባለፈዉ ሳምንት ያሸነፈዉን ጅማ አባቡና ያስተናግዳል ።በአንፃሩ አርባምንጭ በደቡብ ደርቢ በሀዋሳ ተሸንፎ ዉጤት ማጣቱ የሚታወስ ነዉ ።

ይርጋለም ከተማ ላይ ደግሞ የደቡብ ክለቦችን ሊያገናኝ ቀጠሮ ይዘዋል። ሲዳማ ቡና ከወላይታ ዲቻ ።የሚያስገርመዉ ሁለቱሙ ክለቦች በሶስተኛ ሳምንት ጨዋታቸዉ በተመሳሳይ ዉጤት አሸንፈዉ ነዉ(1 ለ0 )በዚህ ሳምንት ላይ ተገናኙ ። ጎንደር ላይ የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስን ከፋሲል ከነማ የሚያገናኝ ሲሆን ለጊዮርጊስ በዉድድር አመቱ የመጀመሪያ የክልል ጨዋታ ፋሲለደስ ስታድየም ላይ ያደርጋል ።በፋሲል በኩል ባለፈዉ ሳምንት ከሜዳ ዉጪ ማለትም አአ ላይ የመጀመሪያዉ ሶስት ነጥብ ከኢትዮጱያ ቡና ማግኙቱ የሚታወስ ነዉ ።በጊዮርጊስ በኩል ደግሞ ሌላዉን የከተማዉን ክለብ መከላከያን ሶስት ግቦችን በማግባት ያለመሸነፈ ጉዞን ያስቀጠለበት የሶስተኛዉ ሳምንት ጨዋታ ነበር።

15319572_1248212688583489_873172360_n

በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታድየም ደግሞ አዳማ ከነማ ከኢትዮጱያ ቡና የሚያደርጉት ጨዋታ ነዉ ። አዳማ ለአአ ቅርብ ከመሆኑ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ ተመልካቹች ወደ አዳማ ይጓዛሉ ተብሎ ይጠበቃል ።ሌላዉ ካላቸዉ የተፍካካሪነት መንፈስም ጨዋታዉ የሚጠበቅ ነዉ ።በባለፈዉ ሳምንት ጨዋታችዉ ሁለቱም ክለቦች በተመሳሳይ ጎል ተሸንፈዉ እንደነበር የሚታወስ ነዉ 1 ለ0 በሆነ ዉጤት ኣዳማ በዲቻ፤ ቡና በፋሲል ነበር ሽንፈት ያስተናገደበት ። በምስራቋ ኢትዮጱያ ድሬዳዋ ላይ ሁለቱ የመስተዳደር ክለቦችን ያገናኛል ።ድሬዳዋ ከተማ ከአአ ከተማ አአ ላይ ደግሞ ሌላ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ ።በ9 ሰአት መከላከያ ከወልድያ ከተማ ።መከላከያ በሊጉ የመጀመሪያ ሶስት ነጥብ ለማግኙት የሚያደርገዉ ጨዋታ ሲሆን በወልዲያ በኩል ደግሞ ማሸነፍ ከቻለ አአ ላይ የመጀመሪያዉን ነጥብ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል ። ከዚኛዉ ጨዋታ በመቀጠል 11:30 ላይ ኢትዮጱያ ንግድ ባንክ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ያገናኛል ።ንግድ ባንክ በሊጉ ምንም ያላሸነፈ ክለብ ሲሆን በኤሌክትሪክ በኩል ባለፈዉ ሳምንት ነጥብ ተጋርቶ የወጣ መሆኑ የሚታወስ ነዉ ።የተመጣጠነ ፍክክር ይጠበቅበታል ተብሎ የሚካሄድ የአራተኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ ነዉ። በክልል የሚካሄድ ሁሉም ጨዋታዎች ዘጠኝ ሰአት የሚካሄድ ናቸዉ ።

በ ዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.