ዓሳን ቤት ለቤት ለማምረት የሚያስችል ፕሮጀክት ተግባራዊ ሊደረግ ነው

0
975

በሀገሪቷ ያሉ ሃይቆች፣ ወንዞችና ግድቦችን በአግባቡ ከመጠቀም ባለፈ ማንኛውም ጓሮ አሳን ለማምረት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት እየተደረገ ነው።

የእንስሳት እና አሳ ሀብት ሚኒስትር ደኤታ ዶክተር ገብረእግዚአብሄር ገብረዮሃንስ፥ የአሳ ልማት አሁን ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ወደ ተግባር መገባቱን ተናግረዋል።

ከሚተገበሩት ስራዎች ውስጥም ያሉትን ሀይቆች፣ ወንዞች እና ግድቦች በአግባቡ በመጠቀም የሚለው ቀዳሚው ነው ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ በቀላሉ ህብረተሰቡ በጓሮው አሳን እንዲያመርት ማድረግም ይገኝበታል ሲሉም ተናግረዋል።

እነዚህን ሀሳቦችን መሰረት ያደረገ መረሃ ግብር እየተዘረጋ ቢሆንም በሚፈለገው ደረጃ ተግባራዊ እየተደረገ አይደለም ተብሏል።

ሆኖም ግን ዛሬ በይፋ የተቋቋመው የኢትዮጵያ አኳ ካልቸር ማህበር በዚህ ረገድ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ታምኖበታል።

ማህበሩ በዘርፉ የተሰማሩ ምሁራን እና ባለሙያዎችን የያዘ ሲሆን፥ በቀጣይ በርካታ ባለሀብቶችን እና ህብረተሰቡን በማሳተፍ የአሳ ምርቱን የሚያሳድግ ይሆናልም ተብሏል።

በዚህ ስራም ማንኛውም ነዋሪ በጓሮው አንድ ሜትር በእንድ ሜትር ጉድጓድ ጀምሮ እንደ አቅሙ ኩሬዎችን በማዘጋጀት አሳን የሚያመርትበት ስርዓት ይፈጠራል።

በዚህ ዘርፍ መሰማራት የሚፈልግ ሰውም አስፈላጊውን መረጃ በመጠየቅ ወደ ስራ መግባት እንደሚችልም በመድረኩ ላይ ተገልጿል።

 

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.