የሶስተኛ ሳምንት የ2009 ኢትዮጱያ ፕሪሚየም ሊግ ዉጤቶች

0
1155

የሶስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች መክፈቻ ጨዋታ የነበረዉ ቅዳሜ በ11:30 በአአ ስታድየም የተካሄደዉ ኢትዮጱያ ቡና ከፋሲል ከነማ በነበረዉ ጨዋታ ነበር ።ስታድየም ሁለቱም ደጋፊዎች የደመቀ እና የተለየ አደጋገፍ በፋሲል በኩል ተመልክተናል ።በጨዋታዉም ፍፁም የበላይነት በፋሲል ከነማ በኩል የነበረ ነበር። በዉጤቱም በኤርሚያስ ሀይሌ ብቸኛ ግብ ፋሲል 1 ለ0 በማሸነፈ በሊጉ የመጀመሪያዉን ድል አስመዝግባል። . ሌሎች ጨዋታዎች እሁድ እለት የተካሄድ ሲሆን ሁለቱ አአ ላይ ቀሪ ሰባት ጨዎታዎች ደግሞ በክልል የተካሄድ ናቸዉ። . . ወደ ይርጋለም ያቀናዉ ድሬዳዋ በስንዴይ ሙቱኩ ግብ ሲዳማ 1 ለ0 አሸንፎ እንዲወጣ አድሮጎል።

በደቡብ ደርቢ ሀዋሳ ላይ አርባምንጭ ከነማን ያስተናገደዉ ሀዋሳ ከነማ ከበረኛዉ ክብርአለም ዳዊት እልፈት በኋላ የመጀመሪያዉን ሶስት ነጥብ በፍሬም ሰለሞን ሁለት ግቦች አሳክቷል። . ጅማ ላይ ንግድ ባንክን ያስተናገደዉ ጅማ አባቡና በዳዊት ተፈራ እና በኦሜ መሀመድ ግቦችን በማስቆጠር 2 ለ 0 አሸንፎል።በንግድ ባንክ በኩል በሊጎ ባደረጋቸዉ ጨዋታዎች ሁለቱንም ያላሸነፈ ክለብ ነዉ።

በሊጉ በዚኛዉ ሳምንት የመጀመሪያ ሽንፈቱኑ ያስተናገደዉ ደግሞ አዳማ ከነማ ነዉ ቦዲቲ ላይ ተጉዞ በወላይታዲቻ ተሸንፎል የግቡም ባለቤት አላዛር ፋሲካ ነዉ።በወላይታ በኩል በተጫወታቸዉ ሁለት ጨዋታ ያልተሸነፈ ክለብ ነዉ።  ወልዲያ ላይ የተጋዘዉ ደደቢት ያለምንም ግብ ነጥብ ተጋርቶ መጥቶል።በሊጉ የዚህ ሳምንት ግብ ያልተቆጠረበት ጨዋታ። . አአ ላይ በዘጠኝ ሰአት ደግሞ የነበረዉ ጨዋታ አአ ከነማ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ነዉ። ጨዋታዉም 1 ለ1 የተጠናቀቀ ሲሆን ግብ አግቢዎቹ በአአ ከነማ በኩል ፍቃድ አለሙ ሲያስቆጥር በኤልክትሪክ በኩል ዳዊት እስጢፋኖስ የግብ ባለቤት ነበር። ሌላዉ በሊጉ ሲጠበቅ የነበረዉ ጨዋታ ኢትዮጱያን በአፍሪካ መድረክ በሚወክሉ ክለቦች በኩል የተደረገ ጨዋታ ነዉ። ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመከላከያ ጨዋታዉ እንደተጠበቀዉ ባይሆንም በሁለተኛ አጋማሽ የተሻለ የነበረዉ ጊዮርጊስ በደጋፊዎቹ ታጅበዉ 3 ለ0 በማሸነፈ በሊጉ እስካሁን ካልተሸነፎ ክለቦች አንድ ሆናል።የግቦቹ ባለቤትም አብድል ከሪም ኒካ አዳና ግርማና ሳላዲን ሰኢድ ናቸዉ።

አሁንም የደረጃ ሰንጠረዥን ቅዱስ ጊዮርጊስ በዘጠኝ ነጥብ ሲመራ አንድ ቀሪ ጨዋታ ያለዉ ወላይታ ዲቻ በስድስት ነጥብ ይከተላል ፤በዚህ ሳምንት ሸንፈት ያስተናገደዉ አዳማ ደግሞ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦል። በሰንጠረዥ ግረጌ ደግሞ የሚገኙ ክለቦች ደግሞ 13ተኛ ላይ 15 ተኛ የ ተቀመጡት ሶስቱ ክለቦች በጎል ክፍያ ተበላልጠዉ ሁሉም በአንድ ነጥብ ተቀምጠዋል ።ኢትዮጱያ ቡና መከላከያ አርባምንጭ ከነማ ናቸዉ።16 ተኛ ላይ ደግሞ ማሸነፈ ያልቻለዉ ንግድ ባንክ በ ዜሮ ነጥብ ተቀምጦል። ጌታነህ ከበደ በመጀመሪያ ሳምንት ባገባቸዉ ሶስት ጎሎች ከአዳነ ግርማ ጋር በኩል ደረጃ ተቀምጠዋል ሌላዉ በዚህ ሳምንት ሁለት ግቦችን ያስቆጠረዉ ፍሬዉ ሰለሞን ጨምሮ ሳላዲን ሰኢድ፣ አላዛር ፋሲካና ፍቃዱ አለሙ በሁለት ግብ ይከተሏቸዋል።

በ ዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.