የ2009 አ .ም ኢትዮጱያ ፕሪሚየም ሊግ የሶስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች

0
1084

የ2009 አ .ም ኢትዮጱያ ፕሪሚየም ሊግ የሶስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች . . በሊጉ በእለተ ቅዳሜ ህዳር 17 በ11:30 በአአ ስታድየም በሚጀመር ጨዋታ የሶስተኛ ሳምንት ጨዎታዎች ይቀጥላሉ ።

ብቸኛዉ የቅዳሜ ጨዋታ ኢትዮጱያ ቡና ከፋሲል ከተማ የሚያደርጉት ተጠባቂ ጨዋታ ነዉ፤ስለዚህ ጨዋታ የተወሰነ ነገር እንበላቹ:: በሊጉ እስኳሁን ያልተገናኙት ቡናና ፋሲል ነገ የመጀመሪያ የሊግ ጨዋታቸዉን እርስ በርስ ያደርጋሉ ።ፋሲል ዘንድሮ ሊጉኑ መቀላቀሉን ልብ ልንለዉ ይገባል ።

15175552_1236882489716509_620694420_n

ያለፎት ሳምንት ዉጤታቸዉን ብንመለከት ኢትዮጱያ ቡና በመጀመሪያ ሳምንት በደደቢት 3 ለ0 የተሸነፈ ሲሆን በመከላከያ ደግሞ አቻ የተለያየባቸዉ ዉጤቶቹ ናቸዉ ።በፋሲል በኩል የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታዉ በሲዳማ 1 ለ0 መሸነፎ የሚታወስ ነዉ ነገር ግን የሁለተኛ ሳምንት ጨዋታ ከወላይታ ዲቻ የነበረዉን ጨዋታ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ አልተደረገም ። በሊጉ ሁለቱም ክለቦች ማሸነፍ አልቻሉም በነበራቸዉ ሳምንታት ጨዋታ ስለዚህ ቡና በአንድ ነጥብ ፋሲል በ0 ነጥብ ላይ ሆነዉ የሚያደርጉት ጨዋታ ነዉ። በፋሲል በኩል ሆነዉ የቀድሞ ክለቦቻቸዉን ኢትዮጱያ ቡና የሚገጥሙ ተጫዎች ሰለሞን ገ /መድህን ፣አቡዱራማን ሙባረክ አና ኤዶም ይጠቀሳሉ።ቡና በኩል የለም ::

ሌላዉ በጨዋታዉ የሚጠበቀዉ በሁለቱም ክለቦች ዘንዱ የሚኖረዉ የደጋፊዎች ብዛት በአአ ስታድየም የሚጠበቅ ይሆናል ።የሁለቱም ክለቦች ደጋፊ የሚያመሳስላቸዉ ተኳዥ ደጋፊ መሆናቸዉእና የድጋፍ አሰጣታቸዉ ለጨዋታዉ የተለየ ድምቀት ይሰጣሉ ተብሎም ይጠበቃል ።

15227893_1236930819711676_173019151_n

በተያያዘም የፋሲል ከነማዉ አሰልጣኝ ዘማርያም ወ/ጊዩርጊስ በህመም ላይ እንደሆነ እና ህክምናዉን ለማድረግ ከሀገር ዉጪ ሄዶ መታከም እንዳለበት ሀኪሞች የነገሩት ሲሆን ነገር ግን ከህክምናዉ ከ 1 ሚሊየን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ ተናግራል ።እናም ድረገፃችንም ለ ዘማርያም የተሻለ ህክምና አግኝቶና ጤንነቱ ተመልሶ ክለቡኑ እንዲመራ ከወዲሁ እንመኛለን ። እሁዱ የሚደረጉ ሌሎች የሊጉ ጨዋታዎች አምስት ጨዋታዎች ክልል ላይ ሲካሄዱ ሁለቱ ደግሞ አአ ላይ ይካሄዳሉ . ይርጋለም ላይ ሲዳማ ከድሬዳዋ ከነማ ሶዶ ላይ ወላይታ ዲቻ ከአዳማ ከነማ ሀዋሳ ላይ ሀዋሳ ከነማ ከአርባምንጭ ከነማ ጅማ ላይ ጅማ አባቡና ከኢትዮጱያ ንግዱ ባንክ አዲስ አበባ ላይ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ አዲስ አበባ ከነማ ወልዲያ ላይ ወልዲያ ከደደቢት ሁሉም ጨዋታዎች ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት እና አአ ላይ በ11:30 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመከላከያ በይዉ ይካሄዳል ።

በ ዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.