የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የነበሩት ወ/ሮ አዲሴ ዘለቀ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።

0
1077

ወ/ሮ አዲሴ ዘለቀ ተረፈ በመደበኛ  የስራ  ገበታቸው  ላይ እያሉ  ባደረባቸው ድንገተኛ ህመም በተወለዱ በ48 አመታቸው ህዳር 6፣2009 ማረፋቸውን የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በላከው መግለጫ አመልክቷል።

ወ/ሮ አዲሴ  ዘለቀ  ከአባታቸው  ከአቶ ዘለቀ ተረፈ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ሙሉ ጫኔ 1961 በደብረ  ማርቆስ ተወልደው የመጀመሪያ ደረጃ  ትምህርታቸውንም በዚያው  ተከታትለዋል። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአዲስ ዘመን ከተማ  ከተከታተሉ በኃላ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በስራ አመራር፣ ሁለተኛ  ዲግሪያቸውን ደግሞ  በኢክስኪዩቲቭ ቢዝነዝ አስተዳደር ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ  አግኝተዋል።

ወ/ሮ አዲሴ ዘለቀ ተረፈ በሙያቸው በአማራ  ክልል በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ከ1980 ጀምሮ ማገልገላቸውን ከምክር ቤቱ የደረሰን መግለጫ  ያመለክታል።

ወ/ሮ አዲሴ ዘለቀ በአማራ ክልላዊ  መንግስት በምዕራብ ጎጃም ዞን በባህር ዳር የምርጫ  ክልል ብአዴን ኢህአዴግን በመወከል  በ5ኛው ብሄራዊ  ምርጫ ለምክር ቤት አባልነት  ተወዳድረው በማሸነፍ ከ2008 ዓ.ም እስከ ዕለተ ሞታቸው  ድረስ  የምክር ቤቱ አባልና የትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል በመሆን የወከላቸውን ህዝብ በታማኝነትና  በቅንነት ማገልገላቸውንም  ምክር ቤቱ  ገልጿል።

የአንዲት ሴትና ወንድ ልጅ እናት የሆኑት ወ/ሮ  አዲሴ  ዘለቀ  የቀብራቸው ስነ  ስርአት  ህዳር 7፣2009 ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት በባህር ዳር ድባንቄ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.